የስራ ላይ ስነ- ምግባርን በአግባቡ በመተግበርየተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል ይገባል

አዲስ አበባ 07/01/2015 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለተቋሙ መካከለኛ አመራሮች ስነ -ምግባራዊ አመራር፣የስራ ላይ ስነ ምግባር እና የጥቅም ግጭትን የተመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ስራ አስፈፃሚዋ ወ/ሪት ኤልሳቤጥ በየነ እንደገለጹት አመራሩ የስራ ላይ ስነ-ምግባር መርሆዎችን በውል ተገንዝቦ ተግባራዊ በማድረግ የተቋማትን የአግልግሎት አሰጣጥ ሂደት የተቀላጠፈ ማድረግ፣ ሙስናንና ብልሹ አሰራርን በመታገል እንደ ሀገር የተያዘውን የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እድገት ለማሳካት ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡

ስራ አስፈፃሚዋ አክለውም ሙስናና ብልሹ አሰራርን በመከላከል የተቋማትን የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደትን የሚያዘምን አመራር መፍጠር ሁሉን አቀፍ እድገትን ለማስመዝገብ የሚጫወተውን ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም ከስልጠናው በኋላ አመራሩ የስራ ላይ ስነ-ምግባር መርሆዎችን፣ስነ-ምግባራዊ አመራርን እና የጥቅም ግጭትን በውል ተገንዝቦ በመስራት የተጣለበትን ሃላፊነት መወጣት ይኖርበታል ብለዋል፡፡

Share this Post