ማህበራዊ ግንኙትን ማጠናከር ላይ መስራት ለኢኮኖሚ ማደግ ወሳኝ ሚና አለው/መላኩ አለበል

አዲስ አበባ 11/01/2015 ዓ.ም(ኢ.ሚ) በቅርብ ጊዜ በጎርፍ ምክንያት ቤታቸው ፈርሶ ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ወገኖች ቤት ሰርቶ ለማስረከብ የሚያስችልየመጀሪያ ምዕራፍ ዝግጅት ተካሄደ፡፡

በተፈጥሮ አደጋ የመኖሪያ ቤታቸው ለፈረሰባቸው የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 የአማኑኤል አካባቢ ነዋሪዎች ነው ዛሬ የግንባታ ማስጀመር ኘሮግራም የተካሄደው።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል አደጋው በደረሰባቸው ወገኖች ማዘናቸውን ገልፀው የአንድ ሀገር ኢኮኖሚን ለማሳደግ የሰው ሀብት ልማትና ማህበራዊ ግንኙነትን ማጠናከር ላይ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አደጋው ለደረሰባቸው የአካባቢው ነዋሪዎች መኖሪያ ቤት ገንብቶ እንደሚያስረክብ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ባለፈው በጀት ዓመት ከ28 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ በማድረግ ዜጎችን የቤት ባለቤት ማድረግ፣ የመስሪያ ቦታና የመንቀሳቀሻ ገንዘብ በመስጠት የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል ያሉት ሚኒስትሩ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመሆን የነዋሪዎቹን ቤቶች በጥራት በመገንባት ለተጠቃሚዎች ለማስረከብ ጥረት እንደሚደረግ ገልፀው ሁሉም ዜጋ ለሰው ሀብት ልማትና ማህበራዊ ግንኙነትን መጠናከር የበኩሉን ድርሻ በመወጣት የመረዳዳትና አብሮ የማደግ ባህሉን እንዲያሳድግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዝግጅቱ ላይም የኢንዱስትሪ ሚኒስትር እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ አቶ ዧንጥራ አባይ ፣የ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ስራ አስፈጻሚ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

Share this Post