የማምረት አቅም አጠቃቀም የአለካክ ስልቶች ላይ የጋራ ግንዛቤ መፍጠር ያስፈልጋል፡፡

አዲስ አበባ 13/01/2015 ዓ.ም (ኢሚ) የአንዱስትሪ ሚኒስቴር በኮንስትራክሽን ግብዓቶች ዘርፍ ለሚገኙ ቀለም አምራች ፋብሪካዎች በምርትና ቴክኒክ ኃላፊነት ላይ ላሉ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰቷል፡፡

የአምራች ኢንዱሰትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክትር አቶ ስለሺ ለማ በስልጠናው ላይ እንደገለፁት የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለሀገራዊ ልማት ያለው ሚና ወሳኝ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ የድጋፍና ክትትል ስራዎች በስፋት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ በኢኮኖሚው ዕድገት ውስጥ የሚጠበቅበትን ሀገራዊ ድርሻ እንዲወጣና ጉልህ ሚና እንዲኖረው ለማድረግና የምርት አቅምን ለማሳደግ የማምረት አቅም አጠቃቀም የአለካክ ስልቶች የጋራ ግንዛቤ መፍጠር ያስፈልጋልም ነው ያሉት ፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ከአቅም አጠቃቀም ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የመለየት እና አቅም አጠቃቀምን ለማሳደግ የሚያስችሉ አሰራሮችን መዘርጋት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የምርት ማደግ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረውም አቶ ስለሺ አስረድተዋል፡፡

የሚ/መ/ቤቱ የተኪ ምርቶች ተወዳዳሪነት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ሺበሺ ስዩም በበኩላቸው የአምራች እንዱስትሪውን ዘርፍ የማምረት አቅምን ለማሳደግ እንደስራ ክፍል በግብ ደረጃ የተያዘ ዕቅድ ከመሆኑም በተጨማሪ በፋብሪካዎች የማምርት አቅም አጠቃቀምና አለካክ የምርት ሒደቱን በበላይነት በሚመሩትና በሚቆጣጠሩት ሙያተኞች ቀጠተኛ አስተዋፅኦ እንዳለቸው በማመን ስልጠና መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡

ስልጠናው የአምራች ኢንዱስትሪውን አቅም አጠቃቀምን ሊያሳንሱ የሚችሉ ችግሮችን መለየትና በተለዩት ላይ የእርምት እርምጃ በመውሰድ የማምረት አቅም አጠቃቀም ለማሻሻል መሆኑም ጠቁመዋል፡፡

የማምረት አቅም አጠቃቀም አለካክ ስርዓት ተበጅቶ ወጥነት እንዲኖረው ለማድረግ፣ አቅም አጠቃቀም ለማሻሻል ስልጠናው እንደሚጠቅምም አቶ ሺበሺ ገልፀዋል፡፡

Share this Post