የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፖርኮች የግብርና ምርት ብክነትን ለመቀነስ ከፍቸኛ አስተዋፆ አላቸዉ /አቶ መላኩ አለበል/

ጥር 16/2015ዓ.ም (ኢ.ሚ )የኢንዱስትሪ ሚንስቴር ሚንስትር ክቡር አቶ መላኩ አለበል በርሊን የጀርመን አፍሪካ አግሪ-ቢዝነስ ፎረም ላይ በመገኘት ከUNIDO ጋር ዉይይት እያደረጉ ነዉ።

ሚንስትሩ በፓናል ውይይቱ ላይ አምራች ኢንዱስትሪ የግብርና ምርት ብክነትን ለመቀነስ ያለውን አስተዋፆ በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።

በተለይ ስራ የጀመሩት 3 የተቀናጁ ኢንዱስትሪ ፓርክ እና በዙሪያቸው ያሉ የገጠር ሽግግር ማዕከላት ግብዓት በማቅረብ፣ በግብርና ወቅት፣ ምርት በሚሰበሰብበት፣ ወደ ገበያ በሚከፋፈልበት እና እሴት በሚጨመርበት ወቅት ቴክኖሎጂ በመጠቀም የግብርና ምርት ብክነት እንዲቀንስ ያደርጋልም ሲሉም ክቡር አቶ መላኩ አለበል ተናግረዋል።

Share this Post