አምራች ኢንዱስትሪውን ውጤታማ ለማድረግ በቅንጅት መስራት ይገባል / አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ/

ጥር 18/2015 (ኢ.ሚ) "ኢትዮጵያ ታምርት" ሀገራዊ ንቅናቄ በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች እና የዘርፉ ተዋናዮች በተገኙበት ተካሄዷል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ብሉልታ የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ በቅንጅት መስራት እንደሚገባም በንቅናቄ መድረኩ ላይ ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም አምራች ኢንዱስትሪዎች ውጤታማ ሆነው የማምረት አቅማቸውን ለማሳደግ በፋይናንስ፣ በመሰረተ ልማት መሟላት፣ በገበያ ትስስር ዘርፉ ውጤታማ እንዲሆኑ በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል።

ሀገራዊ ንቅናቄው ከተጀመረ በኋላ በዘርፉ አበረታች ውጤቶች መታየታቸውንም ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ እንድሪስ በበኩላቸው ለአምራች ኢንዱስትሪው ትኩረት በመስጠት እና አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን በመሳብ፣ ነባሮቹን በማጠናከር ለኢንቨስትመንት ዘርፉ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ ነው ብለዋል።

Share this Post