ኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ በሰቆጣ ከተማ ተካሄደ

ጥር 20/2015 ዓ.ም (ኢ.ሚ) በሰቆጣ ከተማ በኢንዱስትሪው ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ ከማዕድን ዘርፉ ማህበረሰቡን እና ሀገርን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚረዳ የኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ የምክክር መድረክ ከባለሃብቶችና ከባለድርሻ አካላት ጋር ተደረገ።

በንቅናቄ መድረኩ ላይ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ምክትል አሥተዳዳሪና የኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ ሹመት ጥላሁን እንደገለጹት ዋግ የበርካታ ፀጋዎች ባለቤት መሆኗን ገልጸው እስከ አሁን አከባቢውን የሚቀይር ሥራ አለመሰራቱን አንስተው ዋግ ውስጥ የወርቅ ፣የብረት እና የከበሩ ማዕድናት በስፋት እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡ በቀጣይም በተጀመረው ኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ በዘርፉ ለውጥ ለማምጣት በትኩረት ይሰራልም ብለዋል፡፡

የአማራ ክልል ኢንቨስትመንት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ይሄነው ታደለ በአማራ ክልል ካሉት ዞኖች እስከአሁን ፀጋዎቿን ያልተጠቀመች ቢሆንም በቀጣይ ግን በእንስሳት ሃብት ፣በብረት ማዕድንና በቱሪዝም ዘርፋ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

Share this Post