በበጀት ዓመቱ አማራጭና ታዳሽ ሀይል አጠቃቀምን በተመለከተ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ሰፊ ግንዛቤ ተፈጥሯል

ነሀሴ 27/2016 ዓ.ም(ኢ.ሚ) ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አማራጭና ታዳሽ ሀይልን ከመጠቀም አንፃር እያከናወነ ያላቸውን ተግባራት በ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት በተካሄደው የኢትዮጵያ ታምርት ዐውደ ርዕይ ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ከማስተዎወቅ ባለፈ

በአፋርና ሶማሌ ክልል ላይ የተከሰተውን ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ የተባለውን ወራሪ አረምን ወደ ሀይል ምንጭነት መቀየር እንደተቻለ በተግባር አሳይቷል፡፡ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ መጤ አረምን ለስሚንቶ ፋብሪካዎች ለድንጋይ ከሰል ግብዓት ከመጠቀም በተጨማሪ ሌሎች ኢንዱስትሪዎች እንደ አማራጭ የሀይል ምንጭነት እንዲጠቀሙበት የሚያስችል ሰፊ ግንዛቤ መፈጠሩን የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ዳዊት አለሙ ገልጸዎል።

ይህን ተከትሎም ዐውደ ርዕዩን የጎበኙ የኢንዱስትሪው ባለድርሻ አካላት ዕሴት የተጨመረባቸውን የባዮ ማስ ምርቶች ለመጠቀም ከፍተኛ ፍላጎት ስላሳዩ ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር በጋራ መስራት የሚቻልበትን ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን አቶ ዳዊት አክለዎል።

Share this Post