በ2016 የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 3 ቢሊየን የገበያ ትስስር ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል (አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ)

የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከግንቦት 1 እስከ 5/2016 ዓ.ም ለሚካሄደው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2016 አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ እና የኤክስፖ አላማ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ማነቆ በመፍታት ዘላቂና ተወዳዳሪ ማድረግ በዚህም አነስተኛ እና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎችን መመገብ የሚችል መሪ ኢንዱስትሪዎችን መፍጠር ፣ ከውጪ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን በአገር በቀል ምርቶች ለመተካት አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ እና ወጪ ምርትን ማጎልበት እንደሆነ የኢንዱትሪ ሚኒስትር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ ገልጸዋል፡፡

በኤክስፖ 200 በላይ በቆዳና ቆዳ ውጤቶች፣ ጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ምግብና መጠጥ፣የእንጨትና እንጨት ውጤቶች፣ የኬሚካልና የግንባታ ዕቃዎች ፣የአውቶ ሞቢልና ማሽነሪ፣ የኤልክትሮኒክስና የኤሌክትሪካል አምራች ኢንዱስትሪዎች ተሳታፊ እንደሚሆኑ የጠቆሙት አቶ ታረቀኝ ከነዚህም መካከል ሰማንያዎቹ አነስተኛና መካከለኛ ቀሪ 120ዎቹ ከፍተኛ ኢንዱትሪዎች እንደሆኑ አብራርተዋል፡፡

ለአምስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው ኤክስፖ ላይ ከ50 ሺ በላይ የአገር ውስጥና የውጪ ሀገር ጎብኚዎች ተሳታፊ እንደሚሆኑና ወደ 3 ቢሊዮን የገበያ ትስስር ይፈጠራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሚኒስትር ዴኤታው አክለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2016 የአምራች ኢንዱስትሪው እድገት ከየት ወደ የት እንደሆነ አመላካች የሆን የፎቶ ኤግዚቢሽን ፣የተለያዩ አምራች ኢንዱስትሪዎች የምርት ሂደታቸውን በተግባር የሚያሳዩበት፣ የተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የዘርፉ ተዋናዮች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚወያዩበት የፓናል ውይይቶችን እንደሚያካትት ተጠቁሟል፡፡

ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post