የኢንዱስትሪ ዘርፍ የ8 ነጥብ 2 በመቶ እድገት ማስመዝገቡ ተገልጸ

ጥር 22/ 2015(ኢ.ሚ) የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ተካሂዷል።

በመድረኩም የበጀት ዓመቱ የስድስት ወራት ዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚና የዘርፎች አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።

ሪፖርቱን ያቀረቡት የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ዶክተር ፍጹም አሰፋ ኢንዱስትሪ ዘርፉን በተመለከተ ባለፉት ሁለት ዓመታት በውስጣዊ ችግሮችና ውጫዊ ጫናዎች ከፍተኛ ፈተና ገጥሞት የነበረ ዘርፍ መሆኑነስ ጠቅሰው ዘንድሮ የተሻለ አፈጻጸም ማሳየቱን ተናግረዋል።

ዘርፉ ባለፉት ስድስት ወራት በርካታ ፈተናዎችን ተቋቁሞ የ8 ነጥብ 2 በመቶ እድገት ማስመዝገቡንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዘንድሮ በ7 ነጥብ 5 በመቶ እድገት የሚመዘግብበት መሆኑን የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም እንደሚያመላክት ተጠቁሟል።

በ2014 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 6 ነጥብ 4 በመቶ እድገት ማስመዝገቡን አስተውሰው በዘንድሮው በጀት ዓመት ደግሞ በ7 ነጥብ 5 በመቶ እድገት የሚመዘገብበት መሆኑን የስድስት ወራት አፈፃፀሙን መነሻ በማድረግ ዶክተር ፍጹም አብራርተዋል።

Share this Post