በዙሪያችን ያለውን እምቅ ዐቅም መለየት ወሳኝ ዕውቀት ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

መስከረም 11 /2015ዓ.ም አዲስ አበባ (ኢ.ሚ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዙሪያችን ያለውን እምቅ ዐቅም መለየት ወሳኝ ዕውቀት መሆኑን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመካከለኛው አዋሽ በ20 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ እየለማ የሚገኝ የጥጥ እርሻን ጎብኝተዋል።

አካባቢው በአንድ ወቅት በጎርፍ የመጥለቅለቅ አደጋ ተጋላጭ እንደነበርም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አስታውቀዋል።

በአካባቢው ያለውን ፍራፍሬ የማብቀል ዐቅም ለመጠቀምም የተሻሻለ የመስኖ አሠራር በመተግበር ላይ ይገኛል ብለዋል።

Share this Post