Content ግልፅ ጨረታ ቁጥር 007/2016
በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአየር ንብረት ለዉጥ ሴክተር ሪፎርም ፐርፎርማንስ ፕሮጀክት ለአምስት አምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ የኢነርጂ ኦዲት ስራ እና የማማከር አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ከላይ ለተገለጹት ግዥዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታ እንዲሣተፉ ይጋብዛል፡፡
1.በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ እና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው የዘመኑን ግብር
ስለመክፈላቸው ማረጋገጫ የሚያቀርቡ፤
2.የዘመኑን ግብር የተከፈለበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
3.ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
4.በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ወይም e-GP
ለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5.ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የአምራች ኢንዱስትሪዎች የኢነርጂ ኦዲት ስራ እና የማማከር አገልግሎት ዝርዝር መግለጫ /TOR/ መሠረት በማድረግ ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
6.በጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10‚000 /አስር ሺህ ብር /በባንክ በተረጋገጠ /cpo/ ማስያዝአለባቸው
7.የጨረታ ሰነዱን በመ/ቤቱ website WWW.moi. gov.et ፤ በtelegram ወይም በemil ማግኘት
የሚትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
8.ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ኦሪጅናልና ኮፒዎችን ለየብቻ በትልቅ
ፖስታ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ለብቻው በአንድ ፖስታ በማሸግና የድርጅቱ ማህተም
በማድረግ ታሽጎ ማቅረቢ አለበት፡፡
9.ጨረታው ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመ/ቤቱ web site w w w.moi. gov.et አየር
ላይ ከቆየ በኃላ መጋቢት 10 /2016ዓ.ም ከጧዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾች
ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡
10.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
11.ለተጨማሪ መረጃ መ/ቤቱ የሚገኘው 4 ኪሎ ከቱሪስት ሆቴል ጀርባ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 122
በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥሮች 011-858-31-51 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር