Jul 2025

የኢትዮጵያ እና የኳታር ግንኙነት ለሰላም፣ ለብልፅግና እና ዘላቂ ልማት በጋራ ራዕይ ላይ የተመሰረተ ነው ( አቶ ሃሰን መሃመድ)

ሰኔ 23/2017ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ ሃሰን መሃመድ በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር እና በአፍሪካ ህብረት የኳታር መንግስት ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ሳድ ቢን ሙባረክ አል ናይሚ በፅፈት ቤታችው ተቀብለው አነጋገሩ

የድንጋይ ከሰልን በባዮ ማስ መተካት በመቻላችን እጅግ በጣም ተጠቃሚ ሆነናል(የክብር ዶ/ር ብዙአየሁ ታደለ)

ሰኔ 23/2017 ዓ.ም (ኢ/ሚ) የናሽናል ስሚንቶ ፋብሪካ ባለሀብት የክብር ዶ/ር ብዙአየሁ ታደለ ቀደም ሲል ለፋብሪካቸው በግብአትነት ሲጠቀሙት የነበረውን የድንጋይ ከሰል በፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ ባዮ ማስ መተካት በመቻላቸው ተጠቃሚ እንደሆኑ ገልጸዋል ፡፡

የስሚንቶ ፋብሪካዎች አማራጭ ሀይልን ለመጠቀም ዝግጁ መሆን አለባቸው(ኢ/ር አክሱማዊ ዕቡይ)

ሰኔ 23/2017 ዓ.ም(ኢ/ሚ) የፓን አፍሪክ ግሪን ኢነርጅ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር አክሱማዊ ዕቡይ ሀገሪቱ የጀመረችውን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ዕውን ለማድረግ ሁሉም አምራች ኢንዱስትሪ አማራጭ ሀይልን ለመጠቀም ዝግጁ መሆን እንደሚገባው ገልፀዋል ፡፡

የስሚንቶ ፋብሪካዎች የፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ አረምን በሰፊው መጠቀም ከቻሉ የውጭ ምንዛሬ ብክነትን በከፍተኛ ደረጃ ማስቀረት ይቻላል (አቶ ሀርቢ ቡህ)

ሰኔ 22/2017 ዓ.ም(ኢ/ሚ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ የስሚንቶ ፋብሪካዎች በናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የተጀመረውን የባዮ ማስ አጠቃቀም በስፋት መጠቀም ከቻሉ የውጭ ምንዛሬ እጥረትን በከፍተኛ ደረጃ ማስቀረት እንደ ሚቻል ገለጹ፡፡

ከፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ አረም የፀዱ መሬቶች ዓመቱን በሙሉ በሰብል መሸፈን አለባቸው(አቶ ዳዊት አለሙ)

ሰኔ22/2017 ዓ.ም(ኢ/ሚ) ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ አረም ከፀዳ በኋላ እንደ ገና ስለሚበቅል የፀዱ መሬቶችን ዓመት እስከ ዓመት በሰብል መሸፈን እንዳለባቸው በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአየር ንብረት ለውጥ ሴክተር ሪፎርም ፐርፎርማንስ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት አለሙ ገለጹ፡፡

በአምራች ኢንዱስትሪዎቻችን አማራጭ ሀይል መጠቀም በመቻላችን ከሶስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ከብክነት ማዳን ችለናል(አቶ ሀሰን መሀመድ)

ሰኔ 21/2017 ዓ.ም(ኢ/ሚ)የኢፌድሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ አረምን እንደ ሀይል አማራጭነት መጠቀምን አስመልክቶ በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ የልምድ ልውውጥ ሰሚናር አካሄደ፡፡ ድሬደዋ ከተማ ተገኝተው በመርሀ ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የመሠረተ ልማትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒ

ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ' የተባለውን መጤ አረም ለሲሚንቶ ማምረቻ በኃይል አማራጭነት መጠቀም የሚያስችል ጥናት ተጠናቆ ወደ ስራ ተገባ

ሰኔ 21/2017(ኢሚ) በሳይንሳዊ ስሙ 'ፕሮሶፒስ ጁሊ ፍሎራ' የተባለውን መጤ አረም ለሲሚንቶ ማምረቻ በኃይል አማራጭነት ለመጠቀም ሲደረግ የነበረው ጥናት ተጠናቆ ወደ ተግባር ገብቷል።

በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የተካሄዱ በርካታ የጥናትና ምርምር ውጤቶች ተግባር ላይ መዋላቸው ተገለጸ

ሰኔ 21/2017 ዓ.ም(ኢ/ሚ)የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሚልኬሳ ጃጋማ በዘርፉ ከተሰሩ ችግር ፈች ጥናትና ምርምሮች ውስጥ ከ80% በላይ የሚሆኑት ተግባር ላይ እንደዋሉ ገለጹ፡፡

በድህረ_ እውነት አለም ላይ ለትውልድ የሚበጀውንና ምርትና ምርታማነት የሚያሳድገውን መረጃ ተደራሽ ማድረግ መቻል ትልቅ አርበኝነት ነው (የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል)

ሰኔ 21/2017ዓ.ም (ኢሚ) የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በ2017 ዓ.ም በበላይነት ሲመራቸው ለነበሩ ሁለት ትላላቅ አለም አቀፍ ሁነቶች መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የሚዲያና ኮሙኒክሽን ተቋማት ባደረገው የእውቅና እና ምስጋና መርሃ-ግብር ላይ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ እንደ ሀገር የተካሄዱ የኢትዮጵያ ታምርት ኤ

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለሚዲያ ተቋማት የምስጋና መርሀ ግብር አካሄደ ።

ሰኔ 18/2018ዓ.ም(ኢሚ) ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከረሃብ ነፃ ዓለም እና የኢትዮጵያ ታምርት ኤከስፖ 2017 ስኬታማነት ጉልህ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ተቋማት፣ ለተጠሪ ተቋማትና ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች የዕውቅና ሽልማት አበረከተ፡፡

ለአለም አቀፍ ሁነቶቹ መሳካት ሚስጥር በመናበብና ጠንክሮ በመስራት ነው (የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል )

ሰኔ 18/2017 ዓ.ም (ኢሚ)የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በ2017 ዓ.ም በበላይነት ሲመራቸው ለነበሩ አለም አቀፍ ሁነቶች መሳካት አስተዋፅኦ ላደረጉ የሚዲያ ተቋማት እና ባለድርሻ አካላት የእውቅና እና ምስጋና መርሃ ግብር አካሂዷል።

በ2017 በጀት አመት ከአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የወጪ ምርት የተገኘው ገቢ የ8 በመቶ እድገት አሳይቷል::

ሰኔ 17/2017 ዓ.ም (ኢሚ) ከአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ በ2017 በጀት አመት 11 ወራት 474.9 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ በአፈጻጸሙ 289.8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወይም የዕቅዱ 61 በመቶ ማግኘት መቻሉን በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የወጪ ምርቶች ተወዳዳሪነት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘሪሁን አበበ

የአምራች ኢንዱስትሪ ባለሀብቶች የዘርፉ ከፍተኛ አመራሮች የሚያደርጉላቸው ድጋፍና ክትትል እንደ ሚያበረታቸው ገለጹ

ሰኔ 17/2017 ዓ.ም (ኢ.ሚ) የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚገኙ ታላላቅ ፋብሪካዎችን ጎበኙ፡፡ በጉብኝታቸው አግኝተው ያነጋገሯቸው የኢንዱስትሪ ባለሀብቶች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እያደረገላቸው ያለውን ድጋፍ በማመስገን የዘርፉ ከፍተኛ አመራሮች የሚያደርጉላቸው

ቢሾፍቱ ከተማን የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ እና የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየሰራን ነው ( አቶ አለማየሁ አሰፋ )

ሰኔ13/10/2017 ዓ.ም (ኢሚ) ቢሸፍቱ ከተማ በባህልና በቱሪዝም መስህብ የበለፀገች ከመሆኗ ባለፈ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ከፍተኛ ዕድገት እያስመዘገበች መሆኑን የቢሸፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ ገለፁ ፡፡

የኢንዱስትሪ ከፍተኛ አመራሮች ቢሸፍቱ ከተማ የሚገኙ አምራች ኢዱስትሪዎችን ጎበኙ።

ሰኔ13/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ፤የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ፣ የቢሸፍቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ እንዲሁም የኦሮሚያ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊዎች እና የክልሉ የስራ ኃላፊዎች በከተማዋ የሚገኙ አምራች ኢንዱ

ሃገራዊ ዕድገትን የምናረጋግጠው አምራች ኢዱስትሪውን በመደገፍ ነው (አቶ መላኩ አለበል)

ሰኔ 13/2017 ዓ.ም (ኢሚ) ፈቃዱ ፀጋዬ ቢዝነስ ግሩፕ የቤት እቃዎች እና የመኪና ሞተር መገጣጠሚያ፤ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር አቶ መላኩ አለበል መርቀው ከፈቱ፡፡ ሚኒስትሩ በምረቃው መርሃ-ግብሩ ላይ እንደገለፁት መንግስት የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ሃገራዊ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ከፍ እንዲል ከፍተኛ ትኩ

7ኛው የአግሮ ፉድ ሾው ፎረም ተካሄደ

ሰኔ 13/2017 ዓ.ም (ኢሚ) 7ኛው የአግሮ ፉድ እና ፕላስቲክ፣ህትመት፣ፓኬጅ የምግብና ቡና ሾው ተካሄ። ፎረምን በንግግር የከፈቱት በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የመሰረተ ልማትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሐመድ ፎረሙ የማሽነሪ፣ የቁሳቁስ እና የማሸጊያ ማሳያ መሆኑን በመጥቀስ በኢትዮጵያ እየታየ ላለው

ፋብሪካው በዓመት ከአንድ ሚሊዮን ካሬ ሜትር ስኩዌር በላይ ፎርም ወርክ ማምረት ይችላል፡፡

ሰኔ 13/2017 ዓ.ም (ኢሚ)የኤች ኬ ቢዝነስ ግሩፕ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በዓመት ከአንድ ሚሊዮን ካሬ ሜትር ስኩዌር በላይ ፎርም ወርክ የማምረት አቅምም ያለው በመሆኑም የኮንስትራክሽን ዘርፉን የፎርም ወርክ ፍላጎት በአስተማማኝ ደረጃ ማሟላት እንደሚችል የኤች ኬ ቢዝነስ ግሩፕ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማ

የሚሰሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች ለአምራች ኢንዱስትሪው ተወዳዳሪነት የሚጨምሩት ፋይዳ ሊኖር ይገባል

ሰኔ12/2017 ዓ.ም(ኢ/ሚ)የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲና ማስፈጸሚያ ስትራቴጅዎች ዙሪያ ለሁለት ቀናት የሰጠው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ በስልጠናው መጨረሻ የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሚልኬሳ ጃጋማ በዘርፉ ተመራማሪዎች የሚሰሩ የጥናትና ምርምር

የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ለማሳደግ ለማሽነሪ ኢንዱስትሪ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል።

ሰኔ11/2017 ዓ.ም (አ/ሚ) የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በሚሰጠው የፖሊሲና ስትራቴጅ ስልጠና መርሀ ግብር ተገኝተው የማሽነሪ ስትራቴጅን በተመለከተ ገለፃ ያቀረቡት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተኪ ምርቶች ተወዳዳሪነት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ መሳይነህ ውብሸት ዘርፉን ለማሳደግ ለማሽነሪ ኢንዱስትሪ ትኩረት ሰጥ

የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ አመራሮች ውጤታማ ስራ እንዲሰሩ በዘርፉ ፖሊሲዎችና ስትራቴጅዎች ዙሪያ ጥልቅ ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል። (ዶ/ር ሚልኬሳ ጃጋማ)

ሰኔ11/2017 ዓ.ም (ኢ.ሚ) የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ፖሊሲና ስትራቴጅዎች ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡ የስልጠና መርሀ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሚልኬሳ ጃጋማ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ አመራሮች ውጤታማ ስራ እን

Jun 2025

ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የሥነ ምግባር ግንባታ እና የሙስና መከላከል ስራዎቹን አስገመገመ፡፡

ሰኔ 10/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢፌዲሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በመሆን በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሥነ ምግባር ግንባታ እና የሙስና መከላከል ስራዎቹ በፌደራል የሥነ ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የድጋፍና ክትትል ቡድን ግምገማ አካሄደ ፡፡

የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ የወደፊት እጣ ፈንታ በመቅረጽ ረገድ የቋሚ ኮሚቴው ሚና የላቀ ነው ( አቶ ሀሰን መሃመድ )

ሰኔ 09/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለኢንዱስትሪና ማዕድን ቋሚ ኮሚቴ አመራሮችና አባላት በአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ የማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት እያካሄደ ነው። በሚኒስቴሩ የመሠረተ ልማትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታው አቶ ሀሰን መሃመድ የግንዛቤ ማስጨበጫ

የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፉን መልካም ስነ ምግባርን በተላበሱ አመራሮች መመራት ለምርታማነትን ቁልፍ ድርሻ አለው (አቶ ሀዱሽ ሀለፎም)

ሰኔ 7/2017 ዓ.ም(ኢ/ሚ)የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀዱሽ ሀለፎም የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ አመራሮች ጥሩ ስነ ምባር መላበስ ምርታማነትንና የማምረት አቅምን እንደሚያሳድግ ገለጹ፡፡

ሙስናን ለመግታት ከታችኛው መዋቅር እስከ ፌዴራል ድረስ ተቋማት በቅንጅት መስራት አለባቸው(ወ/ት ኤልሳቤጥ በየነ)

ሰኔ 7/2017 ዓ.ም(ኢ/ሚ) የኢፌድሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማትና ከክልል የኢንዱስትሪ ቢሮዎች ጋር የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ፎረም ምስረታ አካሄደ፡፡ የፎረሙን ምስረታ አስመልክቶ ገለፃ ያቀረቡት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስነ ምግባር መከታተያ ስራ አስፈፃሚ ወ/ት ኤልሳቤጥ በየነ ሙስናን ለመግታት ከታ

የቀርቀሃና የእንጨት ውጤቶች ሀገራዊ ፋይዳቸው ዘርፈ ብዙ ነው ( አቶ መሳይነህ ውብሸት)

ሰኔ 6/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ክራኬቲቭ ካታሊስት ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማ በእንጨት፣ በቀርቀሃ እና በጥሬ ዕቃ ማምረቻ እሴት ሰንሰለቶች ላይ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

አምራች ኢንዱስትሪዎች ቀጣይነት ያለው ዕድገት ኖሯቸው ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የደንበኞቻቸውን ፍላጎት የሚያሟላ ምርት ማምረት አለባቸው ።

ሰኔ 5/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት፣ ከጂ አይ ዜድና ሶሊዳሪዳድ ጋር በመቀናጀት ለሀያ ጨርቃጨርቅና አልባሳት ፋብሪካ ተወካዮች በብሔራዊ የተቀናጀ የምርት ጥራት መቆጠጠሪያ ስርዓት(National Integrated Production Quality Management S

የተኪ ምርት ስትራቴጂ የአምራች ኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪነት ለማጎልበት እና ለማጠናከር ለሚደረገው ጥረት ጉልህ ሚና አለው።

ሰኔ 4/2017 ዓ.ም (ኢሚ) በሀገር ውስጥ ያለውን አቅም በተገቢው መንገድ በመረዳትና በመጠቀም ረገድ የተኪ ምርት ስትራቴጂው ውጤት ማሳየቱን በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተኪ ምርቶች ተወዳዳሪነት መሪ ስራ አስፈፃሚ የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ መሰሉ አበበ ገልፀዋል ።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተኪ ምርት የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ያተኮረው የግምገማና የምክክር መድረክ ተካሄደ ።

ሰኔ 4/2017 ዓም(ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተኪ ምርት የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ውይይቱን ያቀረቡት በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኬሚካል ውጤቶች ዴስክ ኃላፊ አቶ መሃመድ ጦይብ እንደገለፁት ተኪ ምርት ዙሪያ በኢትዮጵያ እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች ውጤት እየታየበት ነው ብለዋል ።

የተኪ እና የውጪ ምርቶችን ውጤማነት ለማሳደግ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ነው (አቶ መሳይነህ ውብሸት)

ሰኔ 4/2017ዓ.ም (ኢሚ) የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአምራች ኢንዱስትሪ የተኪ ምርት ስትራቴጂ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያላቸው ኢንዱስትሪዎች፣ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ተጠሪ ተቋማቱ ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ነው ።

ምርታማነት ውጤታማ የሚሆነው ጊዜን፣ ጉልበትንና ካፒታልን አጣጥሞ መስራት ሲቻል ነው ( አቶ ዮናስ መኩሪያ )

ሰኔ 3/2017ዓ.ም (ኢሚ)የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ምርታማነት ምንድን ነው በሚል ፀንሰ ሃሳብ ከክልል እና ከተማ አሰተዳደር ኢንዱስትሪ ቢሮዎች ፣ ለአምራቾች ፣ ለተጠሪ ተቋማት እና የኢዱስትሪ ሚኒስቴር ሰራተኞች ስልጠና ሰጠ ።

የአምራች አዱስትሪው አቅም አጠቃቀም መለካት ለሃገራዊ ኢኮኖሚዊ ዕድገት እና ልማት ወሳኝ ነው (አቶ ዮናታን ተስፋዬ)

ሰኔ 3/2017ዓ.ም (ኢሚ)የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለክልል እና ከተማ አሰተዳደር ኢንዱስትሪ ቢሮዎች ፣ ለአምራቾች ፣ ለተጠሪ ተቋማት እና የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሰራተኞች የማምረት አቅም አጠቃቀም አለካክ ላይ የግንዛቤ መስጨበጫ ስልጠና ሰጠ ። ስልጠናውን የሰጡት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ኢ

የተኪ ምርት 2018ዓ.ም እቅድ እና የማምረት አቅም አጠቃቀም ስልጠና ማስጀመሪያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው።

ሰኔ 3/2017ዓ.ም(ኢሚ) በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተኪ ምርቶች ተወዳዳሪነት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ መሳይነህ ውብሸት እንደገለፁት አንድ ዕቅድ አንድ አፈፃፀም በሚል መሪ ሃሳብ አየሰራን እንገኛለን ሰልጠናው የዚህ መሪ ሃሳብ አንድ አካል ነው ብለዋል።

የጉሎ ዘይት በአለም አቀፍ ደረጃ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው እፅዋት ነው(አቶ ሃሰን መሃመድ )

ግንቦት 28/9/2017ዓ.ም (ኢሚ) ጆርጅ ሹ ኀ.የተ የግ.ማ ከዚህ ቀደም የራሱን ኢንዱስትሪ ፓርክ በመገንባት በኢትዮጵያ በቆዳ፣ ጫማና በኮንስትራክሽን ስራ ተሰማርቶ የሚገኝው ካፓኒ ነው ፡፡ አሁን ላይ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የጉሉ ዘይት ፋብሪካ በመገንባት ወደ ስራ የገባ ሲሆን በዚህ ስራ ላይ ከኢንዱስ

አምራች ኢንዱስትሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በዘርፉ የሚካሄዱ የጥናትና ምርምር ስራዎች ወሳኝ መሆናቸው ተገለጸ

ግንቦት 28/2017 ዓ.ም(ኢሚ) በአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የምርምርና ቴክኖሎጅ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍቃዱ አሸኔ አምራች ኢንዱስትሪዎች ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የግድ በጥናትና ምርምር መደገፍ እንዳለባቸው ገልፀዋል ፡፡ ዶ/ር ፍቃዱ አምራች ኢንዱስትሪዎች በየወቅቱ የሚገጥሟቸውን ተግ

የመንግስት ማንኛውም ኢኮኖሚዊ ማህበራዊ እንቅስቃሴ አካባቢ ጥበቃን ታሳቢ ያደረገ ነው ( አቶ ሃሰን መሃመድ)

ግንቦት 28/9/2017ዓ.ም (ኢሚ)የኢዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሃሰን መሃመድ ፅዱ ኢትዮጵያን ባህል ማድረግ በሚል መሪ ቃል የተካሄደውን ሁለተኛውን የአካባቢ ብክለት መከላከል አገራዊ ንቅናቄ የመስጀመሪያ መርሐ ግብር ፓናል ውይይት ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለፁት ማንኛውም ኢኮኖሚዊ ማህበራዊ እንቅስቃሴ አካ

የክልል አመራሮች በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ አቅም ያላቸውን የውጭ ኢንቨስተሮች ለመሳብ አበክረው መስራት አለባቸው(አቶ መላኩ አለበል)

ግንቦት 28/2017 ዓ.ም(ኢሚ) የኢፌድሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለሚገኙባቸው አራት የክልል መስተዳደሮች የመኪና ርክክብ ስነስርዓት አካሄደ፡፡ በርክክብ ስነስርዓቱ ወቅት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል የክልል አመራሮች በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ አቅም ያላ

ኢንዱስትሪ ለአንድ ሃገር ቁልፍ ጉዳይ ነው(ኢንጅነር ምንዳዬ ይርጋ)

ግንቦት 26/2017ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ የአመራር አቅም ግንባታ መርሃ ግብር የጥናት ሰነድ ያቀረቡት የካይዘን ኢንስቲትዩት ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ምንዳዬ ይርጋ እንደገለፁት የአንድ ሃገር ኢንዱስትሪ ውጤታማና ተወዳዳሪ የሚሆነው በፈጠራና በቴክኖሎጂ እድገት ፤ የሰለጠነ የሰው ሃይል አጠቃቀም፤ የተግባር ልህቀ

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የክልሉ ኢንቨስትመንት ፍሰትን እንዲነቃቃ አድርጓል(ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ)

ግንቦት 26/2017(ኢሚ) የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የአማራ ክልል ኢንቨስትመንት ፍሰትን የበለጠ እንዲነቃቃ ማድረጉን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ተናገሩ። በክልሉ የኢንቨስትመንት ፍሰት በተለይ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ በብዛትም ሆነ በጥራት እየተሻሻለ መጥቷል ብለዋል። ንቅናቄው የተለያዩ

አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ተወዳዳሪነት ለማሳደግና ምርትና ምርታማነቱን ለመጨመር የአመራር አቅም ግንባታ ወሳኝ ነው(አቶ ሃሰን መሃመድ)

ግንቦት 26/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የአምራች ኢንዱስትሪ አመራር አቅም ግንባታ ፕሮግራም ማስጀመሪያ መረሃ ግብር የበቃ ኢንዱስትሪ አመራር ለላቀ ተወዳሪነት በሚል መሪ ቃል አምራች ኢንዱስትሪ ካውንስል ለተመረጡ 50 ተፅዕኖ ፈጣሪ ኢንዱስትሪዎች ተለይተው የአመራር አቅም ግንባታ የትግበራ ማስጀመሪያ መድረክ ተካሄደ ፡፡

የአመራር አቅም ግባታ ስልጠና ማሰጀመሪያ መረሃ ግብር እየተካሄደ ነው ።

ግንቦት 26/2017ዓ.ም( ኢሚ) የኢንዱስትሪ አመራር አቅም ግንባታ " የበቃ የኢንዱስትሪ አመራር ለላቀ ተወዳዳሪነት "በሚል መሪቃል በአምራች ኢንዱስትሪ ካውንስል በተመረጡ ሃምሳ ተፅዕኖ ፈጣሪ ኢንዱስትሪዎች ተለይተው የትግበራ ማስጀመሪያ መረሀ ግብር በካይዘን የልህቀት ማዕከል እየተካሄደ ነው ።

የአምራች ኢንዱስትሪውን ችግር በመፍታት የዘርፉን ሀገራዊ የኢኮኖሚ ድርሻ ከፍ ሊያደርጉ የሚችሉ ማሻሻያዎች እየተከናወኑ ነው (አቶ ሀሰን መሐመድ)

አዲስ አበባ ግንቦት 25/2017 (ኢ•ሚ) የኢትዮ ቤልጄም ቢዝነስ ፎረም ተካሄደ፡፡ የኢትዮ ቤልጄም ቢዝነስ ፎረም ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የመሰረተ ልማትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሃመድ ኢትዮጵያ ለኢንዱስትሪያላይዜሽን ያላትን የማያወላውል ቁርጠኝነት እና በለው

በሲዳማ ክልል ለእንስሳት ምርታማነት ተጨማሪ አቅምን የሚፈጥር የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብርካ ተመረቀ

ግንቦት 24/2017 (ኢሚ) በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ከተማ በሱፐርኦቫ አግሮቴክ ኃ.ተ.ግ.ድ የተገነባ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ተመርቆ በይፋ አገለልግሎት መስጠት ጀምሯል ። ፋብሪካው ከዚህ በፊት ከነበሩት ሠራተኞች በተጨማሪ ከ100 በላይ ወጣቶች የስራ ዕድልን እንደሚፈጥር ተገልጿል። የሲዳማ ክልል

ብሔራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ካውንስል አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍን በመደገፍ እና ችግሮችን በመፍታት ተወዳዳሪ ለማድረግ የተቋቋመ ነው ( አምባሳደር ግርማ ብሩ)

በአምባሳደር ግርማ ብሩ የሚመራው ብሔራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ካውንስል በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ በሚስተዋሉ ችግሮች ዙሪያ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸውን ተጠቅመው እንዳያመርቱ የሚያደርጉ እና ለውጤታማነታቸው እንቅፋት ናቸው በተባሉ ምክንያች ዙሪያ የተዘጋጀ ሰነድ የቀረበ

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ በኢትዮጵያ የቤልጀየም አምባሳደር ዶ/ር አኔሊስ ቨርስቲቼልን በቢሯቸው ተቀብለው አነጋገሩ::

ግንቦት 18/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢንዱስትሪ መሰረተ ልማትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ በኢትዮጵያ የቤልጀየም አምባሳደር ዶ/ር አኔሊስ ቨርስቲቼል በቢሯቸው ተቀብለው አነጋገሩ:: ቤልጂየም እና በኢትዮጵያ መንግስት ጠንካራ እና ዘላቂ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላቸው ያሉ

መንግስት ቆዳ የኤክስፖርት አማራጭና የኢንዱስትሪያላይዜሽን ዋና ዘርፍ እንዲሆን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው(አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ)

ግንቦት15/2017 ዓ.ም(ኢሚ)የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ 14ኛውን የመላ አፍሪካ የቆዳ ንግድ ትርኢትን ከፈቱ፡፡ አዲስ አበባ በሚሊኒየም አዳራሽ የሚካሄደውን የቆዳ ምርቶች ዐውደ ርዕይ የከፈቱት አቶ ታረቀኝ መንግስት ቆዳን የኤክስፖርት አማራጭና የኢንዱስትሪያላይዜሽን ዋና ዘርፍ እን

የኤሌክትሪካል እና ኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን በዓለም አቀፍ ገበያ በጥራት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው፡፡ (አቶ ፀሐዬ ይነሱ)

ግንቦት 13/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለሀገሪቱ እድገትና ልማት የሚያበረክተውን ወሳኝ አስተዋፅዖ ከግምት ውስጥ በማስገባት ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው ምርቶች መካከል አንዱ የኤሌክትሪካል እና ኤሌክትሮኒክስ ምርት መሆኑን በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በተኪ ምርቶች ተወዳዳሪነት መሪ ሥራ አስፈፃሚ የኤሌክትሪ

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ፕሮፌሰር ላውራንስ ፍሪማን በቢሯቸው ተቀብለው አነጋገሩ

ግንቦት 12/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ተንታኝ ፕሮፌሰር ላውራንስ ፍሪማን በቢሯቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡ የውይይታቸው ዋና ትኩረትም በሀገራዊ ዕድገት በተለይም የአምራች ኢንዱስትሪ አሁናዊ ገጽታ እና በዘርፉ ስላሉ ምቹ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ነበረ፡፡

May 2025

አምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የግል ኢንቨስትመንትን በማበረታታት ሁለንተናዊ ብልጽግናን እናረጋግጣለን:: (አቶ ሀሰን መሀመድ)

ግንቦት 8/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢንዱስትሪ መሰረተ ልማትና ግብአት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ ከቻይና ሹኒ (SHUNY) ግዛት ተወክለው የመጡ ባለ ስልጣናትን አወያዩ፡፡

መንግስት በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የውጭ ሀገር ባለሃብቶችን ለማበረታታት ምቹ ፖሊሲና ስትራቴጅ ቀርጿል:: (አቶ ሀሰን መሀመድ)

ግንቦት 8/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢንዱስትሪ መሰረተ ልማትና ግብአት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ አድቫንስድ ከትሬንድ ኤንድ ማይኒንግ (ADVANCED TRADE AND MINING) ድርጅት ተወክለው የመጡ የኳታር ባለ ሀብቶችን ተቀብለው አወያዩ፡፡