የኢትዮ-ጣሊያን ኢንቨስትመንት ትስስር የሚያጠናክር ውይይት ተካሄደ

መጋቢት 03/2016 ዐ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ ከጣልያን ልማት ትብብር ዋና ዳይሬክተር ስቲፋኖ ጋቲ እና ልዑካቸው ጋር የሁለቱን አገራት የኢንቨስትመንት ትስስር በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ኢንዱስትሪያላዜሽንና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር የመንግስታችን የኢኮኖሚ አጀንዳ ዋና ጉዳዮች ናቸው ያሉት አቶ ታረቀኝ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርም ለግቡ መሳካት አስፈላጊውን ፖሊሲና ስትራጂዎችህን አውጥቶ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑንም ጠቁመል፡፡

በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ላይ የጣልያን ባለሃብቶች ሚና ትልቅ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው እንዱስትሪያላዜሽን ለማምጣት በተለይም በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ከተዘጋጁ የህግ ማዕቀፎች በተጨማሪም የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተግባራዊ በማድረግ የተለያዩ ውጤቶች መምጣት መቻላቸውንም አመላክተዋል፡፡

ሁለቱ አገራት በተለያዩ የልማት እና የጸጥታ ሁኔታዎች ላይ ጥብቅ ቁርኝት እንዳላቸው ያነሱት አቶ ታረቀኝ ይህንንም በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ሁለቱ አገራት ለበርካታ አመታት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ትስስር እንዳላቸው የገለጹት የጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ስቲፋኖ ጋቲ ይህንን ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና ፕሮጀክቶች ላይ እያደረጉ ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡

በርካታ የጣሊያን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የቡና ኢንዱትሪው ዘርፍ መሰማራታቸውን ለአብነት ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ በቀጣይም በቡና ፣ ፋሽን፣ ቆዳ፣ጨርቃጨርቅ እና ሌሎች የኢንቨስትመንት አማራጮች በመሰማራት ለዜጎች የስራ እድል የመፍጠር እና በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪላይዜሽን እድገት ላይ በጋራ ለመስራት ፍላጎቱ እንዳላቸው ጠቁመል፡፡

በውይይቱ በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ፣ምቹ ሁኔታዎችና እና የሁለቱን አገራት የኢንቨስትመነት ትስስሮች የሚያሳይ ሰነድ ቀርቧል ፡፡

ይከታተሉን

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post