በተሻሻለ የምግብ ጥራት፣ ደህንነት እና ክትትል ቁጥጥር ማዕቀፍ የተቀናጁ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ማጠናከር ያስፈልጋል(አቶ መላኩ አለበል)

ሚያዚያ 4/2016ዓ.ም (ኢ.ሚ)የተቀናጁ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርኮች የፖሊሲም ሆነ የመሰረተ ልማት ችግሮችን ለመፍታት የሚያግዙ ናቸው፡፡

ከኢንዱስትሪ ክላስተር የሚገኘው ጥቅማ ጥቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚሄድ የውጭ ባለሃብቶችንም ሆነ የሀገር ውስጥ ኢንተርፕራይዞችን የሚያጎለብቱ የኋልዮሽና የፊትዮሽ ትስስሮች እንዲፈጠሩ የሚያግዙ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገልፀዋል፡፡

ለቅድመ-እሴት ሰንሰለቶች የተቋቋሙ የደህንነት እና የመከታተያ ስርዓቶች እና በተቀናጁ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ለምግብ ደህንነት እና የጥራት ደረጃ ላቦራቶሪዎች ስራ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል ያሉት ሚኒስትሩ በአግሮ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ያሉ የንግድ ድርጅቶች በተሻሻለ የምግብ ጥራት፣ ደህንነት፣ክትትል እና ቁጥጥር ማክበር ላይ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ስኬት በብዙ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ነው ያሉት አቶ መላኩ ጥራት ያለው የሀገር ውስጥ እና የውጭ ባለሃብቶችን ወደ ዘርፉ መሳብ፣ የምርቶችን ጥራት ማስጠበቅ፣ ደህንነት እና ክትትል ማረጋገጥ ከፊት የሚጠብቁን ዋና ተግባሮቻችን ናቸው ብለዋል፡፡

የሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት ወሳኝ ነው ያሉት ሚኒስትሩ በዘርፉ ያለውን የፋይናንስ አቅም እና የወጪ ምንዛሬ ችግር ለመፍታት የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡

የተቀናጁ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርኮች አሠራርና ዘላቂነት በኢትዮጵያ ፕሮጀክት የመጀመሪያው የፌዴራል ፕሮጀክት አስተባባሪ ኮሚቴ የውይይት መድረክ ተካሄዷል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

Share this Post