የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የኢትዮጵያዊያን የመቻል አቅም ማረጋገጫ ነው (አቶ ሀሰን መሐመድ)

ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ፣ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች እና የክልል እና ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ቢሮ ሀላፊዎች በተገኙበት በአንድ ጀንበር 700ሚሊዮን ችግኞች በመትከል ማንሰራራት ሀገራዊ አረጓዴ አሻራ መርሃ_ግብር በእንጦጦ ችግኝ በመትከል ተካሄዷል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የግብዓትና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሐመድ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የኢትዮጵያዊያን የመቻል አቅም ማረጋገጫ መሆኑን ጠቅሰው ሁሉም ዜጋ ለሀገራዊ እቅድ ስኬቱ መረባረብ ይኖርበታል ብለዋል፡፡

የላቀ የእድገት ጎዳናን ያረጋገጠች ሀገር ለመጭው ትውልድ ማስረከብ የሚቻለው የአየር ንብረት ለውጥ ሚዛናዊነትን በማረጋገጥ የተፈጥሮን ፀጋ ለመንከባከብ በጋራ መስራት ሲቻል መሆኑን ገልጸው የኢትዮጵያዊያን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ስራ በአርዓያነት ከትውልድ ትውልድ በተግባር የሚወሳ የኢትዮጵያ የብልፅግና አሻራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post