የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ካቀረቡት ጥያቄዎች መካከል፡-
የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ያስገኘው ሰላም እፎያታ አስገኝቷል፡፡
በስምምነቱ መሰረት ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የስምምነት ነጥቦቹ በምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ?
በትግራይ ክልል እየታየ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ ወደግጭት እንዳያመራ ምን እየተሰራ ይገኛል?
መገዳደል፣ መጠፋፋት እና የፖለቲካ ተቃርኖ ዛሬም ዋጋ እያስከፈለን በመሆኑ መንግስትና መሪው ፓርቲ ችግሮችን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተነጋግሮ የመፍታት ባህል ማጎልበት ላይ በተሰሩ ስራች የተገኘ ውጤት ቢብራር?
የመልሶ ማደረጃት ስራ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?
ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ከአሥር ዓመቱ ስትራቴጅክ እቅዱ አንፃር ያላቸው አፈፃጸም፣
በስድስት ወር ውስጥ የመንግስት ወጪና ገቢ ምን እንደሚመስል ቢብራራ?
በተለያዩ ዘርፎች የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን በዘላቂት ለመፍታት በቀጣይ የሚቀመጡ አቅጣጫዎች ላይ ማብራሪያ ቢሰጥ?
በስብሰባው ላይ የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄዎችን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት