አምራች ኢንዱስትሪው የሚፈልገውን የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት በቅንጅት እየተሰራ ነው (ወ/ሮ አበባ ታመነ-

ግንቦት7/2017 (ኢሚ) አምራች ኢንዱስትሪው የሚፈልገውን የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የገለፁት የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃዌ ወ/ሮ አበባ ታመነ በዘርፉ የሚፈልገውን የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማፍራት የሚያስችል ሥርዓት በመዘርጋት ወደ ተግባር ተገብቷል ብለዋል።

መንግስት ተግባራዊ ያደረገውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ወሳኝ የኢኮኖሚ ምሰሶ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

የአምራች ዘርፉ እንደ ግብርና፣ ማዕድን፣ ቱሪዝም እና ሌሎች ዘርፎችን እንዲደግፍ ለማድረግ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተቀርፆ ወደተግባር መገባቱንና ከፍተኛ የሚባል ለውጥ እያመጣ መሆኑን የጠቀሱት ስራ አስፈፃሚዋ ንቅናቄው ኢትዮጵያ ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶችን ማምረት እንደምትችል ያሳየችበት እንደሆነ ተናግረዋል።

በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት የሰለጠነ የሰው ሀይል ወሳኝ ነው ያሉት ወ/ሮ አበባ አምራች ኢንዱስትሪው የሚፈልገውን የሰለጠነ የሰው ሀይል ለመፍጠር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

የሰለጠነ የሰው ሀይል አንዱ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አካል መሆኑን በመግለጽ፤ በዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ የዘርፉ ተማሪዎች በተለያዩ ኩባንያዎች የተግባር ልምምድ እንዲያደርጉ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በአምራች ኢንዱስትሪ ላይ በችግር ፈቺ የምርምር ስራዎች ላይ የሚሳተፉበት እድል መመቻቸቱን ጠቁመዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post