በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ዘላቂ ልማት መፍጥር በሚያስችሉ ዕድሎች ዙሪያ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡
ህዳር 19/2017 ዓ.ም (ኢሚ) ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ዕድገት በመንግስት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችና ውጤታማነት እንዲረጋገጥ ግንዛቤ ለመፍጠር ከቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
በተለይም በዋናነት ዓላማ ያደረገው በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በወጪ ምንዛሬ ግኝት ፣ በተኪ ምርት እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ለውጥ ማምጣት የሚችሉ ኢንዱስትሪዎችን በመለየት ያለባቸውን ችግሮች መፍታት የሚቻልበት ግንዛቤ በውይይቱ ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡