የማምረት አቅም አጠቃቀምን ማሻሻል ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ተቀዳሚ ተግባር ነው ( አቶ መሳይነህ ውብሸት)

ታህሳስ 03 /2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለተጠሪ ተቋማቱ፣ ለምርምር ማዕከላቱ፣ ለክልልና ከተማ አስተዳደር ፣ ለፋብሪካ አመራሮችና ባለሙያዎች የማምረት አቅም አጠቃቀም አመላካቾችና የአለካክ ስልቶች ማንዋል ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ነው።

የተኪ ምርቶች ተወዳዳሪነት መሪ ስራ አስፈፃሚው አቶ መሳይነህ ውብሸት የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የሚሰጣቸው አገልግሎቶችና የድጋፍ ስራዎች ማጠንጠኛ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም አጠቃቀም በማሻሻል ውጤታማነታቸውን ማረጋገጥ ነው ብለዋል።

የኢንዱስትሪዎችን የአቅም አጠቃቀም ለማሻሻል የአምራች ኢንዱስትሪዎችን መሪዎችና ባለሙያዎች ተከታታይነት ያለው የአቅም ልማት ስራ በመስራት ብቁ ማድረግ የዘርፉ ተቀዳሚ ተግባር መሆኑን ገልፀዋል ።

ስልጠናውን የሰጡት የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ምርምር ልማት ማዕከል ተመራማሪ የሆኑት አቶ ዮናታን ተስፋየ ከዚህ በፊት የነበረው የአቅም አጠቃቀም የአለካክ ዘዴ እንደ ተቋም፣ ባለሙያና ኢንዱስትሪዎች (ፋብሪካዎች) የተለያየና ወጥነት የሌለው የነበረ መሆኑን በመጥቀስ የኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት በማሻሻል የዘርፉን እድገት ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ በማድረግ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ለሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚጠበቅበትን ያህል እንዲያበረክት ማስቻል የማምረት አቅም አጠቃቀም ወጥነት ያለው የአለካክ ስርዓት አስፈላጊ በመሆኑ ማንዋሉ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post