በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ስራዎች ተስፋ ሰጪ ስኬቶች ተመዝግበዋል ( አቶ ጥላሁን አባይ)
ጥር 13/ 2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢዱስትሪ ሚኒስቴር የ2017 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የዕቅድ አፈፃፀሙን ለክልልና ከተማ አስተዳደር ፣ ተጠሪ ተቋማት፣ ባለ ድርሻ አካላትና የዘርፍ ማህበራት አቅረቦ እየገመገመ ነው ።
የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን ያቀረቡት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥላሁን አባይ እንደገለፁት መንግስት ለዘርፉ በተሰጠው ልዩ ትኩረት፣ በተሰሩ ቅንጅታዊ ስራዎችና ድጋፎች የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም አጠቃቀም ከአለፉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ ተችሏል፡፡
ዋና ዋና በሆኑ የስራ ማሳያዎች እንደ ውጭ ምንዛሬ ግኝት፣ ተኪ ምርት፣ የአቅም አጠቃቀም፣ የግብዓት አቅርቦትና ሌሎች የዘርፉ ስራዎች ተስፋ ሰጪ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልፀዋል።
በሌላ በኩል በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በፋይናስ በአቅም ግንባታ ፣ በመሰረተ ልማትና በምርምር ስኬታማ ስራዎች በመስራቱ የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ መቻሉን የገለፀፁት አቶ ጥላሁን የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት አፈፃፀም ከ2016 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር ከፍ ያለ መሆኑን ጠቁመዋል ።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት