ኢትዮጵያዊያን በጋራ በአንድነት ከሰራን ድህነትን ማሸነፍ እንደምንችል የዓድዋ ድል ማሳያ ነው/አቶ ሀዱሽ ሀለፎም /

የካቲት 21/6/2017ዓ.ም (ኢሚ) የኢዱስትሪ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በመሆን 129ኛዉ የዓድዋ ድል በዓልን "ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል " በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ስነ ስርዓቶች አከበረ ፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሚኒስቴር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀዱሽ ሀለፎም እንደገለፁት አባቶቻችን ባርነትንና ቅኝ ግዛትን እምቢ ብለው የቋንቋ፤ የኃይማኖት፣ የፆታና የባህል ልዩነት ሳይበግራቸው ወራሪውን የጣሊያን ሠራዊት በዓድዋ ምድር በፍፁም ጀግንነትና በሀገር ፍቅር ስሜት ተፋልመው ድል በማድረግ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አስከብረዋል ሲሉ ግልፀዋል ፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የህዝብ እና የኮምንኬሽን ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ ታመነ እንደገለፁት የዓድዋ ድል የኢትዮጵያውያን የድል በዓል ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም የሚገኙ ጥቁር ህዝቦች ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ለመውጣት ተስፋን የሰነቁበትና መነቃቃትን የፈጠሩበት ታሪካዊ ድል ነው ሲሉ ገልፀዋል ፡፡

ይህን ድል ተከትሎ በቅኝ ግዛት ሥር የነበሩ በርካታ የዓለማችን ሀገራት ከገዥዎቻቸው ነፃ የወጡበትን ቀን የነፃነት ቀን ብለው ሲያከብሩ እኛ ኢትዮጵያውያን ግን የዓድዋ ጀግኖች በከፈሉልን ክቡር መስዋዕትነት ከአፍሪካ በብቸኝነት የድል በዓል የምናከብር ሀገር ሆነናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ወ/ሮ አበባ የኢትዮጵያ ህዝቦች ያለ አንዳች ልዩነት በየዘመኑ የተቃጣባቸውን የውጪ ወረራና የውስጥ አፍራሽ ኃይሎችን ሴራ በመመከት የግዛት አንድነትን ለማስጠበቅና የፀናች ኢትዮጵያን ለማስቀጠል አያሌ መስዋዕትነት ተከፍሏል ይህንን አውቀን ወቅቱ በሚጠይቀውን የሰላም፣ የልማት እና የዴሞክራሲ ግንባታ ስራን ማስቀጠል እንዲሁም ሃገራችንን በኢንዱስትሪ በግብርና በቱሪዝም አድጋና በአለም ጠንካራ ኢኮኖሚ ያላት የበለፀገች ኢትዮጵያ ሆና እንድትታይ ማድረግ ከኛ ትውልድ የሚጠበቅ ነው ሲሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡

Share this Post