በይርጋለም የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፖርክ የህፃናት ማቆያ ተመርቆ ተከፈተ።
የካቲት 21/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢንዱስትሪ መሰረተ ልማትና ግብአት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን እና የሲዳማ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድርና ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ በየነ በራሳ የህፃናት ማቆያ መርቀው ስራ አስጀምረዋል ።
የህጻናት ማቆያ ማዕከሉ መቋቋም የምርትና ምርታማነት መጨመር ፣ የማህበረሰብ ልማት ማጎልበት ያለው ሚና የጎላነው ያሉት የኢንዱስትሪ መሰረተ ልማትና ግብአት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ ለፓርኩ ሰራተኞችና በፓርኩ አካባቢ ለሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ምቹ እና ተስማሚ የስራ አካባቢ በመፍጠር ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ማደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልፀዋል ።
የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን በበኩላቸው የህፃናት መዋያ ስፍራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ በስነ-ምግባር የታነፀ በስነልቦና የዳበር ጤናማና አምራች ዜጋን መፍጠር ይገባልም ብለዋል።
በተለይም በፓርክ ውስጥ ያሉ ሴት ሠራተኞች በወሊድ ምክንያት ከስራ ገበታቸው ውጪ እንዳይሆኑና ውጤታማ ስራ እንዲሰሩ እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል ።
በምርቃቱ ላይ ሌሎች የሚመለከታቸው የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት