ማንበብ ተቋሙን በመረጃ እና በእውቀት በማደራጀት እንደ ሃገር የተጣለብንን ሃላፊነት ለመወጣት ትልቅ አቅም ይሆነናል ( አቶ ሀዱሽ ሀለፎም)
የካቲት 21/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሚኒስትር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀዱሽ ሀለፎም እንደገለፁት ዛሬ በተቋሙ እና በተጠሪ ተቋም ለምትገኙ አመራሮችና ሰራተኞች ያዘጋጀነው የቤተ መፀሐፍት አሰፈላጊነት አጠቃቀም ምን እና እዴት መሆን አለበት የሚለውን የዘርፉ ሰራተኞች በቂ እውቀት እንዲኖራችሁና የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ በአግባቡ እንድታስፍፅሙ በማሰብ ነው ብለዋል።
እንደ ኢዱስትሪ ሚኒስቴር ብዙ ሃለፊነት እና ተልዕኮ አለብን ያሉት አቶ ሀዱሽ ኃላፊነታችንን በብቃት እና በእውቀት ለመወጣት ተከታታይ የአቅም ልማት ስልጠናዎች አስፈላጊ ናቸው ብለን እናምናለን ብለዋል ።
የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መፃህፍት አገልግሎት የቤተ መፃሕፍት ባለሙያ ወ/ሮ አሰቴር ፍሰሃ በበኩላቸው ቤተ መፃሕፍት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መደራጀት እና በሰለጠነ ባለሙያ መመራት አለበት ብለዋል።
ቤተ መፃሕፍት በዓለማችን ላይ ባሉ የዕውቀት ዘርፎች ላይ የተሰሩ ሰራዎች ተደራጅቶና ተሰንዶ ትርጉም ባለው መንገድ የሚቀመጥበት ስፍራ ከመሆኑም ባሻገር ታሪካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ፋይዳ ያላቸው መፃሕፍት የምናገኝበት ቦታ ነው ሲሉ ገልፀዋል ።
በመሆኑም አሉ ባለሙያዋ ቤተ መፃሕፍት ሰናደራጅ የቤተ መፃሐፍት ዓላማ፣ የተጠቃሚ ዓይነቶች፣ የቤተ መፀሐፉ ህንፃ እና የቤተ መፀሐፍት ባሙያዎች ታስቦበት እና ተጠንቶ መቋቋም አለበት ብለዋል ።
በተጨማሪም ቤተ መፃሕፍት ሲቋቋም የተመቻቸና የተፈጥሮ ብረሃን ሊያገኝ የሚችል፣ ለማንበብ ብቻ ሳይሆን በማሰላሰል እና በተመሰጦ ውስጥ ሆኖ ዘና በማለት እውቀት የሚገኝበት ቦታ ነው ብለዋል ።
በአጠቃላይ ቤተመፃሕፍት እንደ የተቋሙ ዓላማ፣ እንደተጠቃሚዎቹ አይነትና እንደሚይዙት የመረጃ ዓይነት ይለያያሉ ሲሉ ገልፀዋል ።
በመጨረሻም ሰልጣኞቹ ሰልጠናው በቂ ግንዛቤና ዕውቀት ያገኙበት እና የማንበብ ክህሎታቸውን ያለበትን ደረጃ በመፈተሽ የንባብ ባህላቸውን የሚያሳድጉበትን መንገድ ለመቀየስ የማንቂያ ደወል ነው ብለዋል ።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት