ዘላቂነት ያለው እና ሁሉን አቀፍ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ለመገንባት እንሰራለን ( ሚልኬሳ ጃገማ(ዶ/ር )

የካቲት 26/2017 ዓ.ም (ኢሚ) አለማቀፉ የቆዳ ህብረት ስራ ( leather working group) በኢትዮጵያ ለሚገኙ የቆዳ ውጤቶች አምራች ፋብሪካዎች ለኤልኮ አቢሲኒያ የቆዳ ፋብሪካ እና ለኤልኮ አዋሻ የቆዳ ፋብሪካ የወረቅ ደረጀ የእውቅና ሰርተፍኬት እንዲሁም ለባቱ የቆዳ ፋብሪካ የብር ደረጃ ያለው የእውቅና ሰርተፍኬት ሰጥቷቸዋል ፡፡

በታዋቂው አለማቀፉ የቆዳ ህብረት ስራ የሽልማት ሥነ ሥርዓት እንግዳ ሆነው የእውቅና ሰርተፍኬቱን የሰጡት የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲዩት ዋና ዳይሬክተር ሚልኬሳ ጃገማ (ዶ/ር ) ናቸው፡፡

ለአምራች ኢንዱስትሪዎቻችን የተሰጠው የእውቅና ሽልማት በቆዳ ኢንዱስትሪ ውስጥ ዘላቂ እና ለአካባቢ ጥበቃ ኃላፊነት የሚሰማቸው ተግባራን በመስራት እና በማከናወን ለሥነ-ምህዳር ተስማሚ ምርትን ከማስተዋወቅ ባሻገር ኢንዱስትሪዎቻችን በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ሆነው እንዲቀጥሉ ያደርጋል ብለዋል ፡፡

አለማቀፉ የቆዳ ህብረት ስራ ተልእኮ ከሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ ሁኔታዎች እንዲሁም ከኢትዮጵያ መንግስት ዘላቂ የኢንዱስትሪ እድገት እና ራዕይ ጋር በትክክል የሚጣጣም መሆኑን ገልፀዋል ፡፡

ዶ/ር ሚልኬሳ አክለውም የተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት ግቦች የኢንዱስትሪ፣ ፈጠራ እና መሠረተ ልማት ስራዎችን ኃላፊነት ባለው መንገድ የምርት እና አጠቃቀም ስርዓት ዘርግተን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል ፡፡

ኦሬሊያ ካላብሮ የተባበሩት መንግስታት የኢዱስትሪል የልማት ድርጅት (UNIDO) ፕሮጀክት ሌዚክ ማናጀር በበኩላቸው የኢትዮጵያ የቆዳ ፋብሪካዎች ይህን አለም አቀፍ እውቅና ያለው አዋርድ ማሸነፋቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያደርጋል ብለዋል ፡፡

አምራች ኢንዱስትሪዎቻችን ያገኙት የእውቅና ሽልማት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እያደገና ለውጥ መምጣቱን የሚያሳይ ነውያሉት ዋና ዳሬክተሩ ሌሎች የሃገርውስጥ ፋብሪካዎች ከእነዚህ አምራቾች ተሞክሮና ልምድ በመውሰድ ውጤታማ እንዲሆኑ መንገድ የሚከፍት ነው ብለዋል ፡፡

በዘርፉ የተካሄደውን ዓለማቀፋዊ ውድድርቨ ውድድር እንዲካሄድ የፋይናስ ድጋፍ ያደረገው የአውሮፓ ህብረት ስለመሆኑ በመርሃግብሩ ላይ ተገልጿል ፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post