የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ፂዮን ኢዱስትሪያል ኢጂነሪግ እና ብረታ ብረት ኢንተርፕራይዝ የመስክ ምልከታ አደረጉ ።

የካቲት 26/2017ዓ.ም (ኢሚ)ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል የፋብሪካ ምልከታ ሲያካሂዱ ለሚኒስትሩ ገለፃ ያደረጉት የፂዮን ኢዱስትሪያል ኢጂነሪግ እና ብረታ ብረት ኢንተር ፕራይዝ መስራች እና ባለቤት የሆኑት አቶ ዮሐንስ ግርማ ናቸው ።

በገለፃው ወቅት አቶ ዮሐንስ እዳሉት ፋብሪካው በ1999 ዓ.ም በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅቶ በ5000 ብር ካፒታል ስራ የጀመረ መሆኑን ገልፀዋል ።

ባለፉት 18 ዓመታት የተለዩ ደረጃዎችን አልፎ ሰልሣ ሚሊየን ብር የሚያንቀሳቅስ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ዞን አንድ ሺህ ካሬ መሬት ላይ ያረፈ ግዙፍ ፈብሪካ ያለው ለመሆን በቅቷል ብለዋል ።

በፋብሪካው የሚመረቱ ምርቶች የምግብ ማቀነባበሪያ ማሽኖች ፣ የዳቦ መጋገሪያና ማቡኪያ ፣ የቡና መቁያ እና መፍጫ፣ የእህል መከኪያ እና ማበጠሪያ ፣ የመኖ መፍጫና ማቀነባበሪያ ፣ የዕቃ ማሽን ክሬን እና የአመነበረድ ማሽኖች እንደሚያመርት ገለፃ አድርገዋል።

ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ስለፋብሪካው ለተደረገላቸው ገለፃ አመስግነው መንግስት ከዚህ በተሻለ እንዲያመርቱና ውጤታማ እንዲሆኑ የበኩሉን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል ።

ፋብሪካው ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሃገር ውስጥ በመተካት እየሰራ ያለው ስራ ተስፋ ሰጪ መሆኑን ለማየት ተችሏል ።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post