ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት እና ለኢንዱስትሪ እድገት ምቹ የሆነች ሃገር ናት ( አቶ ሃሰን መሃመድ)

መጋቢት 3/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሃሰን መሃመድ የሰንሰለት ምግብ ማቀነባበሪያ ኃላፊነቱ የተ.የግ.ማህበር( Pepsico food ethiopia) በኢትዮጵያ ሊሰራ ስላሰበው የኢንቨስትመነት ማስፋፋያ በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ የተቋሙ የኮርፖሬት ጉዳዮች ዳይሬክተር ሚስስ ሜጋና ላክስማን ማክዶናልድ በፅፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ ፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሃሰን እንደገለፁት ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት እና ለኢንዱስትሪ እድገት ምቹ የሆነች ሃገር ናት ፡፡ መንግስት አዳዲስ ኢንቨስትመንቶች በመሳብ አገራዊ የኢኮኖሚ እድገት ለማምጣት ሁለገብ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል ፡፡

ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለው ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት፣ የከተሞች መሰፋፋትና የኢዱስትሪ መሰረተ ልማት እየሰፋ መሄድ ለአምራች ለኢንዱስትሪ ዘርፉ ምቹ የገበያ እድል የሚፈጥር መሆኑን ገልፀዋል ፡፡

ሲቀጥሉም አቶ ሃሰን ሰንሰለት ምግብ ማቀነባበሪያ ኃላፊነቱ የተ.የግ.ማህበር (Pepsico food ethiopia) በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ ኢንዱስትሪ ውስጥ ጉልህ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ሲሆን ሰፊ የስራ እድል የፈጠረ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፋይዳው ከፍተኛ የሆነ አምራች ፋብሪካ ነው ብለዋል ፡፡

የሰንሰለት ምግብ ማቀነባበሪያ ኃላፊነቱ የተ የግ ማህበር( Pepsico food ethiopia) በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ የተቋሙ የኮርፖሬት ጉዳዮች ዳይሬክተር ሚስስ ሜጋና ላክስማን ማክዶናልድ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ስላለው የኢንቨስትመንት ዕድል ስለተደረገላቸው ገላፃ አመስግነው ከኃይል አቅርቦት ከአካባቢ ጥበቃ እንዲሁም ሌሎች የመሰረተልማት ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ እንደሚያገኙ የተገለፀላቸው በመሆኑ መደሰታቸውን ገልፀዋል ፡፡

በሰላሳ ስምንት ሚሊየን ዶላር ካፒታል የተከፈተው ሰንሰለት ምግብ ማቀነባበሪያ ኃላፊነቱ የተ የግ ማህበር( Pepsico food ethiopia) በአማራ ክልል ቡልጋ የሚገኝ ሲሆን የሚያመርታቸውም ምርቶች ሰን ቺፕስ እና ቺቶፕስ እስናክ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን አሁን ላይ ከ አምስት መቶ ለሚበልጡ ኢትዮጵያዊን የስራ እድል መፍጠሩ ታውቋል ፡፡#PepsiCofoodEthiopia

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post