በኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ የተመራ የባለድርሻ አካላት የስራ ኃላፊዎች ቡልቡላ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኘውን ቲኬ ማኒፋክቸሪግ እና ንግድ ኃ.የተ.የግ .ማ የስራ ጉብኝት አደረጉ ።

መጋቢት 4/2017ዓ.ም በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የእድገትና ተወዳዳሪነት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ የተመራ የባለድርሻ አካላት የስራ ኃላፊዎች ቡልቡላ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኘውን ቲኬ ማኒፋክቸሪግ እና ንግድ ኃ.የተ.የግ .ማ የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸው ፋብሪካው እጅግ ዘመናዊ ዲጂታል የመቆጣጠሪያ ሰርዓት የተዘረጋለት መሆኑ በመሰክ መልከታው ለማወቅ ተችሏል ።

ፋብሪካው የጥቁር አዝሙድ ዘይት፣ የአኩሪ አተር ዘይት ፣የሱፍ ዘይትና የፓልም ዘይት ምርቶችን የሚያመርት መሆኑን የገለጹት የቲኪ ፋብሪካዎች ዋና ኦፕሬቲንግ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ለገሠ ዘይቱ ተጣርቶ ከሚውጣው ተረፈ ምርት የገበታ ቅቤ እንዲሆም የእንስሳት መኖ እና የፕላስቲክ ውጤቶችን ያመርታል ብለዋል ።

የድርጅቱ መስራችና ባለቤት ሼክ ቶፊቅ ከድር በበኩላቸው መንግስት ስራ ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ ለተደረገላቸው የቅርብ ክትትልና ድጋፍ አመስግነዋል ።

ቲኬ ማኒፋክቸሪግ እና ንግድ ኃ.የተ.የግ .ማ በ2014 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን አሁን ላይ ሶስት ቢሊየን ብር ካፒታል ያለው ሲሆን ለሁለት መቶ ስራተኞች የስራ ዕድል መፍጠሩንና ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ሲገባ ለአምስት መቶ ዜጎች የሰራ እድል እንደሚፈጥር ታውቋል ።

በመሰክ ጉብኝቱ ላይ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ ከኦሮሚያ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ ከኦሮሚያ ኢንቨስትመንት ኮምሽን፣ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከፍተኛ ስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post