ኢትዮጲያ ከአፍሪካ አንደኛ ስንዴ አምራች ሀገር ሆናለች (ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር)
መጋቢት 11/2017 ዓ.ም (ኢሚ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ በተለይ የኢትዮጲያን ግብርና በሚመለከት በሀገሪቱ ከ 7.7 ሚለየን ሄክታር በላይ የስንዴ ሰብል ተሸፍኗል፡፡
በዚህም 3መቶ ሚለዮን ኩታል ምርት እንደሚጠበቅ የገለፁት ዶ/ር ዐቢይ ኢትዮጲያ ከአፍሪካ አንደኛ ስንዴ አምራች ሀገር ሆናለች ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በታሪኳ አይታ የማታውቀውን እድገት በዚህ ስምንት ወር አስመዝግባለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ
ሰንዴ ብቻ አይደለም በሌሎች ሰብሎች ውጤታማ ሆነናል፤ በተለይ ለውጡን ተከትሎ በቡና ፤ በሻይ በቅባት እህሎች ውጤታማ ሆነናል ፡፡
በቡና ምርት በተለይ ለውጡን ተከትሎ በዓመት 7 መቶ ሚለየን ዶላር ገደማ ዶላር በዓመት ኤክስፓርት ስናደርግ ቆይተናል፡፡
ባለፈው ዓመት 1.4 ቢለየን ዶላር ቡና ኤክስፓርት ተደርጓል፡፡በዘንድሮ ዓመት ባለፉት ስምንት ወራት ከ 1.2 ቢለየን ዶላር በላይ ኤክስፓርት አድርገናል፡፡
በሚቀጥሉት አራት ወራት ውስጥ 2 ቢሊዮን ዶላር ቡና ኤክስፓርት እናደርጋለን ብለዋል፡፡
ኢትዮጲያ ውስጥ ያለው የቡና ኤክስፓርት ውጤታማ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቡና ላይ ስር ነቀል ውጤት መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት