የአምራች ኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪነት እውን ለማድረግ ጥናትና ምርምር ላይ አበክሮ መስራት ያስፈልጋል

መጋቢት 12/2017 ዓ.ም (ኢሚ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በምግብ ምህንድስና ዘርፉ መሪ ተመራማሪና መምህር እንዲሁም በምግብ ደህንነት የተመሰከረለት የምግብ ደህንነት አዋቂ ፕሮፎሰር ሽመልስ አድማሱ ጥናትና ምርምር ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝና ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን በመጥቀስ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የሚጠበቅበትን ሀገራዊ እድገት እንዲያበረክት ከተፈለገ ለጥናትና ምርምር ስራ ልዩ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል።

ጥናትና ምርምር የተለየ መሰጠትን፣ ትጋትንና ራስን ለስራው አሳልፎ መስጠትን የሚጠይቅ በመሆኑ ለዘርፉ እድገት የሚጨነቁ ለሀገር እድገት የራሳቸውን አሻራ ለማሳረፍ የሚተጉ ብቁ ተመራማሪዎችን መርጦ ተልዕኮ በመስጠት ወደ ተግባር የሚቀየር ተጨባጭ ስራ መስራት ተገቢ ስለመሆኑ ተናግረዋል ።

ፕሮፌሰሩ አክለውም ዘርፉን ተቀዳሚ የሀገራችን የኢኮኖሚ ምንጭ ለማድረግ የሚሰሩ ስራዎችን እውን ለማድረግ በአዲስ መልክ ተቀርፀው ወደ ተግባር የገቡ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጅዎችን አፈፃፀም በየጊዜው ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን መገምገምና እያሻሻሉ መስራት ወቅቱ የሚጠይቀው ተግባር መሆኑን በመጥቀስ ተሻሽለው ወደ ስራ የገቡ ፖሊሲዎችንና የማስፈፀሚያ ስትራቴጅዎችን የማስተዋወቅ ስራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post