የኢዱስትሪ ሚኒስቴር ከሚዲያ ተቋማት ጋር የሚዲያ ፎረም ለመመስረት ምክክር እያካሄደ ነው
መጋቢት 12/7/2017ዓ.ም (ኢሚ) የምክክር መድረኩን የኢዱስትሪ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ አስጀምረዋል ።
የሚዲያ ተቋማት የዘርፉን እንቅስቃሴ ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ በዘርፉ የጠነከረና ቀጣይነት ያለው የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ለማስቻል በአምራች ኢዱስትሪ ዘርፉ የተሻለ ውጤት ለማማስመዝገብ ታስቦ በማሰብ የሚዲያ ፎረም ምስረታ ለማካሄድ የውይይት መድረኩ የተዘጋጀ መሆኑ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ ገልፀዋል ።
በምክክር መድረኩ የሚኒስቴር መስሪያቤቱ የኮሙኒኬሽን ስትራቴጅና የኢትዮጵያ ታምርትን የተመለከቱ ሰነዶች ይቀርባሉ።
በምክክር መድረኩ ማጠናቀቂያ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ሚዲያ ተቋማት የጋራ የስራ ስምምነት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት