ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከሚዲያ ተቋማት ጋር የሚዲያ ፎረም ምስረታና የጋራ የመግባቢያ ስምምነት አካሄደ
መጋቢት 12/7/2017ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ ታመነ እንደገለፁት የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን በማስተዋወቅ ለዘርፉ ሁለንተናዊ ዕድገት የሚዲያው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የሚዲያ ፎረም በመመስረት የጋራ የመግባቢያ ስምምነት በማድረግ ይበልጥ ተቀራርቦ መስራት አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ሚዲያው ለዘርፉ የዕቅድ ስኬት ሙያዊ አሰተዋፆኦ እንዲያበረክት ለማስቻል የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ መዘጋጀቱን የጠቆሙት ስራ አስፈፃሚዋ ለስትራቴጅው ተግባራዊነትና ከሚዳያ ተቋማት ጋር የተገባውን ቃል ኪዳን እውን በማድረግ ረገድ ሁሉም የዘርፉ ተዋንያን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
ከሚዲያዎች ጋር ተነቦና ተቀራርቦ መስራት የዘርፉን ስኬቶች አጠናክሮ ማስቀጠል ጉድለቶችን በፍጥነት በማረም አምራቾችን በማስተዋወቅ የእርስበርስ ትስስራቸውን ለማጎልበት፣ በሃገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የዘርፉን ገፅታ ለመገንባት ጉልህ ሚና ያለው መሆኑን የጠቀሱት ወ/ሮ አበባ የዕውቀት ሽግግር ለማምጣት፣ የልምምድ ልውውጥ ለማካሄድ፣ የገበያ መዳረሻዎችን ለማስፋት፣ ዘርፉን የተመለከቱ መረጃዎችን ለማሰራጨት፣ በዘርፉ የሚዘጋጁ ኤግዚቪሽኖችና ኤክስፖዎችን ህዝባዊ ተደራሽነት ለማስፋት እንዲሁም ጠንካራ መሰተጋብራዊ ግነኙነት እዲኖር ለማስቻል የሚዲያ ፎረም ምስረታውና የመግባቢያ ስምምነቱ ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ገልፀዋል ።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት