ሚዲያ ህብረተሰቡ ዘንድ በቀላሉ ተደራሽ ለመሆን ወሳኙ መንገድ ነዉ (አያና ዘውዴ (ዶ/ር)
መጋቢት 12/7/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በእስከዛሬው ጉዞው ለተመዘገበው ስኬት የሚዲያው ሚና ከፍተኛ መሆኑን የጠቀሱት በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊ አያና ዘውዴ (ዶ/ር) ሚዲያው አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ቋሚ የፕሮግራሙ አካል አድርጎ የትንታኔ ስራ በመስራት የዘርፉን ሀገራዊ ጠቀሜታ የማስገንዘብ ስራ መስራት አለበት ብለዋል።
ሚዲያው ለሚሰራው ስራ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመግባቢያ ስምምነቱን መሠረት በማድረግ ለሚዲያ ተቋማት ባለሙያዎች የዘርፉን ፖሊሲ፣ ስትራቴጅዎችና የአሰራር መመሪያዎች በማስገንዘብ በዕውቀት ላይ የተመሰረት ስራ እንዲሰሩ ለማስቻል ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫና የመስክ ምልከታ ስራ የሚያከናውን ስለመሆኑ ገልፀዋል ።
ዶክተር አያና አክለውም የሚዲያ ተቋማት ለጠንካራ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘላቂ እድገትና ውጤታማነት ስኬታማ የኮሙኒኬሽን ተግባራትን እንዲያከናውኑ አሳስበዋል ።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት