የማይክሮ ማሻሻያው በአምራች ኢንዱስትሪው ላይ የምርት መጠን እንዲጨምር አድርጓል፡፡
መጋቢት 16/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የማክይሮ ማሻሻያው ከተጀመረ ጀምሮ በተለይም በአምራች ኢንዱስትሪው ላይ የምርት መጠን እንዲጨምር ማድረጉን በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተኪ ምርቶች ተወዳዳሪነት ስራ አስፈፃሚ አቶ መሳይነህ ውብሸት ገልፀዋል፡፡
አፈፃፀሙን በትኩረት እየገመገሙ ወደ ተግባር በመግባት በዘርፉ ላይ ለውጥ ማምጣት መቻሉን ጠቁመዋል ፡፡
እንደ ሀገር ሙሉ በሙሉ ባይሆንም ከባለፉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር የወጪ ምንዛሬ በአሁን ሰዓት እንደ ድሮ በአምራች ኢንዱስትሪዎች ዘንድ እንደ ችግር መቅረቡ እየቀነሰ መምጣቱን ያነሱት ስራ አስፈፃሚው በማክይሮ ማሻሻያው ምክንያት በሚፈለገው ልክ እየቀረበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የወጪ ምንዛሬ አቅርቦቱ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች መጠኑ በማደጉ የመለዋወጫ ግብዓቶችን በቀላሉ ከውጭ ሀገር በማስገባት የግብዓት አቅርቦት ሂደቱን ማሻሻሉን አስረድተዋል፡፡
በተለይም አምራች ኢንዱስትሪው ነፃ በመሆን የመለዋወጫ የግብዓት አቅርቦት መጠን በመጨመሩ የምርት መጠን አንዲጨምር ማድረጉን የተኪ ምርቶች ተወዳዳሪነት ስራ አስፈፃሚ አቶ መሳይነህ ውብሸት ገልፀዋል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት