የተኪ ምርትን ለማሳዳግ ውጤታማ የአሰራር ስርዓት በመከተል ዘርፉን ለማሳዳግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡

መጋቢት 17/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማበረታታት የዘርፉን ስራዎች የሚያሳልጡ የአሰራር ስርዓቶች እየተዘረጉ ነው ያሉት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተኪ ምርቶች ተወዳዳሪነት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ መሳይነህ ውብሸት የዘርፉ ችግሮች እየተፈቱ መምጣታቸውን ገልፀዋል፡፡

የተለያዩ ድጋፎች ለአምራች ኢንዱስትሪዎች እየተደረገ መሆኑን የገለፁት ስራ አስፈፃሚው በተለይም ተኪ ምርቶች ከወጪ ከሚገቡ ምርቶች ጋር ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል የተለያዩ ግብዓቶቻቸው ላይ የሚጣሉ ታክሶችን ለመቀነስ በጥናት ላይ የተመሰረተ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ከጉምሩክ ጋር በተያያዘ የመለዋወጫ ግብዓቶችን ሲያስገቡ የሚያጋጥሙ የተለያዩ ችግሮችን ከጉምሩክ ኮምሽን ጋር በመሆን ተቀራርቦ በመስራት እየተፈቱ መሆኑን አቶ መሳይነህ ውብሸት ተናግረዋል::

የተኪ ምርቶችን ለማሳደግ የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ መነሻ በማድረግ አምራች ኢንዱስትሪዎች በሚጨምሩት የእሴት ምጣኔ ልክ ማበራተቻ ማግኘት እንዲችሉ ስትራቴጂ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል ፡፡

ስትራቴጂው ተጠናቆ ወደ ተግባር በሚገባበት ወቅት የእሴት ጭማሪ ምጣኔያቸው ከፍ ያሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያገኙት ማበረታቻ ከፍ ያለ እንደሚሆን የጠቀሱት ስራ አስፈፃሚ ስትራቴጂው በአምራቾች መካከል አውንታዊ ፉክክር በመፍጠር ለዘርፉ ዕድገት ጉልህ ሚና እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡

የተኪ ምርትን ለማሳዳግ ውጤታማ የአሰራር ስርዓት በመከተል ዘርፉን ለማሳዳግ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር የግዢ መመሪያ በጋራ እየተዘጋጀ ነው ያሉት አቶ መሳይነህ በግዢ መመሪያው የሚካተተው አምራች ኢንዱስትሪዎች ምን ያህል እሴት መጨመር አለበቸው የሚለውን አሰራር በመዘርጋት ውጤታማ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በመደግፍ ተወዳዳሪናታቸውን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post