አቶ መላኩ አለበል በኢትዮጵያ የኢራን አምባሳደር ሚስተር አሊ አክባር ረዜል በቢሯቸው ተቀብለው አነጋግሩ ፡፡
መጋቢት 18/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በኢትዮጵያ የኢራን አምባሳደር ሚስተር አሊ አክባር ረዜል በቢሯቸው ተቀብለው ፍሬያማ ውይይት አካሄዱ፡፡
አቶ መላኩ አለበል ኢራን ከኢትዮጵያ ካላት ጉልህ የሁለትዮሽ ግንኙነት በተጨማሪ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ኢንቨስትመንትን በመሳብና በቴክኖሌጂ ትብብር አብሮ ለመስራት መነጋገራቸውን ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ የኢራን አምባሳደር ሚስተር አሊ አክባር ረዜል ከሚያዚያ 19 እስከ ሚያዚያ 23 ቀን 2017 በቴህራን በሚደረገው “ሦስተኛው የኢራን እና የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮንፈረንስ” ላይ እንዲሳተፉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበልን ጋብዘዋቸዋል፡፡
በኮንፍረሱም የኢኮኖሚ እና የንግድ ሚኒስትሮች እንዲሁም የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች የሚሳተፉበት መሆኑን የጠቀሱት አምባሳደሩ የሁለትዮሽ ትብብራችንን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል አስፈፃሚ ፍኖተ ካርታ ለመመስረት የሃሳብ ልውውጥ የሚካሄድበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት