እንደሀገር የተረጋጋ ኢኮኖሚ ለመገንባት ወደ አምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚደረገውን ሽግግር ማጠናከር ያስፈልጋል። (አቶ መላኩ አለበል)

መጋቢት 19/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ታምርት ክላስተሮች ጋር የ2017 በጀት ዓመት የ8 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም የውይይት መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

ለኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ስኬታማነት የተቋማት ቅንጅት መሆኑን የገለፁት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የፋይናንስ አቅርቦት፣ በቂ የግብዓትና የመሰረተ ልማት ከሌለ ማምረት አይቻልም።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ኢንዱስትሪዎችን በማነቃቃት የተዘጉት ኢንዱስትሪዎች ወደ ማምረት እንዲገቡ ማድረጉን ያስታወሱት ሚኒስትሩ የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ የበለጠ ለማሳደግ የተቋማትን ድጋፍና የተናበበ ትብብርን ማጠናከር ይፈልጋል ብለዋል።

እንደሀገር የተረጋጋ ኢኮኖሚ ለመገንባት ወደ አምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚደረገውን ሽግግር ማጠናከር ያስፈልጋል ያሉት ሚኒስትሩ ለዘርፉ እድገት ሁሉም የበኩሉን በመወጣት ኢትዮጵያን ለማሻገር የሚያስችል ኢኮኖሚ መገንባት እንደሚገባም ገልፀዋል ።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post