በአግሮ ኢዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የምግብ ላብራቶሪ መገንባት ወሳኝ ነው ( አቶ ሃሰን መሃመድ)

መጋቢት 19/7/2017ዓ.ም (ኢሚ) የምግብ ጥራት እና ደህንነትን ለማረጋገጥ ብሎም በገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን የምግብ ላብራቶሪ በአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች መገንባት ወሳኝ ነው ያሉት በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የመሰረተ ልማትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሐመድ የምግብ ጥራት እና ደህንነት በኢትዮጵያ ኢዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ለማቋቋም በጣሊያን የልማት ኮርፖሪሽን እና በዩኒዶ ትብብር ከጣሊን ሃገር የመጣ አርተር የሚባለ ኩባንያ የምግብ ጥራት እና ደህንነት ባለሙያዎች ላብራቶሪውን ለማቋቋም እና ወደ ስራ የሚገባበትን መንገድ ለማመቻቸት ከኢዱስትሪ ሚኒስቴር እና ከባለድርሽ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ ፡፡

አቶ ሃሰን እንዳሉት የኢንደስትሪ ሚኒስቴር የኢትዮጵያን የለውጥ አግሮ-ኢንዱስትሪ ስትራቴጂ ተግባራዊ ለማድረግ እና የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን ለአነስተኛና መካከለኛ የአግሮ ኢንዱስትሪ ኢንተርፕራይዞች ዕድሎችን በመፍጠር፣ መዋቅራዊ ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ለማምጣት እየሰራ ይገኛል ብለዋል ፡፡

ኢትዮጵያ ወደ መዋቅራዊ ኢኮኖሚ ለውጥ በምታደርገው ጉዞ ይህንን ወሳኝ ሀገራዊ አላማ ለማሳካት በኦፕሬሽናል አግሮ ኢንተግሬትድ አዱስትሪ ፓርክ (OS-IAIP) ፕሮጀክት በኩል እንደ UNIDO እና የጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ (AICS) ካሉ አጋሮች ጋር ትብብር ማዕቀፍ መስርተን እየሠራን ነው ብለዋል፡፡

ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የአግሮ ኢንዱስትሪ ላብራቶሪ ከአርተር የምግብ ደህንነት ባለሙዎች ጋር በመተባበር በኦሮሚያ፣ ሲዳማ፣ አማራ እና ትግራይ ውስጥ በሚገኙ አግሮ ኢንዱስትሪ ኢንተግሬትድ ፓርኮች( IAIPs) ውስጥ ላብራቶሪ በማቋቋም እና ጥራት ያለው ምርት ለማምረት እና በሃገር ውስጥም ሆነ በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን እሰራለን ብለዋል ፡፡

በመጨረሻም የጣሊያን የልማት ኢጀንሲ ዋና ኃላፊ ሚካኤል ሞርናአ (ዶ/ር) እንዳሉት ኢትዮጵያ በአግሮ ኢንዱስትሪ ምርቶች ውጤታማ እንድትሆንና ተወዳዳሪ ሆና እንድትወጣ ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ የላብራቶሪ ሰራተኞችን በማሰልጠን እና አስፈላጊውን የመሳሪያ ግብዓት በማሟላት የተለመደ ትብብራችንን እናደርጋለን ብለዋል ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን፡ የኢትዮጵያ የምግብ መድሃኒት ባለስልጣን ፤ የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት፡ እና ሌሎችም ተሳታፊዎች ውይይቱ ምርት እና ጥራትን አስተሳስረን እንድንሄድ ዓለም አቀፍ ልምድና ተሞክሮ ያገኘንበት ነው ብለዋል ፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post