በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በመሬት መንቀጥቀጥ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ተደረገ
መጋቢት 20/2017 ዓ.ም (ኢሚ) በኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአየር ንብረት ለውጥ ሪፎርም ፕርፎማንስ ፕሮጀክት በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ።
በክልሉ አሚባራ ወረዳ የተደረገው ድጋፍ ማህበራዊ ሃላፊነትን ከመወጣት አንፃር የታቀደውን እቅድ መሰረት ያደረገ እና የ2017 ኢድ_ አልፈጥር በዓልን ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።
ፕሮጀክቱ ወደ ስራ ከገባበት ጊዜ አንስቶ በአፋርና በሶማሌ ክልሎች ለሚገኙ አቅም ለሌላቸው ሙስሊም ማህበረሰብ ታላቁን የረመዳን ወር አስመልክቶ ማፍጠሪያ የሚሆን አስፈላጊ ድጋፍ እንደሚያደርግ የገለፁት የአየር ንብረት ለውጥ ሪፎርም ፕርፎረማንስ ሴክተር ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ዳዊት አለሙ ይህም ማህበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት በዘለለ በህብረተሰቡ መካከል ጥብቅ ትስስርን ይፈጥራል ሲሉ ጠቁመዋል።
የዘንድሮውን የድጋፍ መርሃ ግብር ለየት የሚያደርገው በአፋር ክልል የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ መከሰቱን ተከትሎ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ 445 አባዎራዎች በገንዘብ 1.5 ሚሊዮን ብር የሚገመት የሩዝ፣ ፓስታ፣ ዱቄት እና የምግብ ዘይት እንደተለገሰ ጠቁመዋል።
በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከታህሳስ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባጋጠመ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከ10 ሺ በላይ አባወራዎች በህዝብ ደረጃ በአጠቃላይ ከ 53 ሺ በላይ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው የገለፁት የክልሉ ዞን 3 አስተዳደሪ አቶ አብዲ አሊ ችግሩን ለመቅረፍም ከተለያዩ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር በጥምረት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በአስፈላጊው ሰዓት ደርሶልናል ያሉት አስተዳዳሪው የችግሩ ስፋት ከግምት ውስጥ በማስገባት ሌሎችም አካላትም የበኩላቸወን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
የክልሉ ኢንዱስትሪ እና ኢንሸስትመንት ቢሮ ኃላፊ አይሻ ያሲን በበኩላቸው ወቅቱ የፆም ወቅትና በቀጣይም የሚከበረውን የኢድ አልፈጥር በአልን በደስታ እንዲያከብር ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት