ድጋፉ በአስፈላጊው ሰዓት የተደረገ ድጋፍ ነው ( በአፋር ክልል አሚባራ ወረዳ ዳይዶ ሳይት ተፈናቃዮች)
መጋቢት 20/2017 ዓ.ም (ኢሚ) በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ያጋጠመውን የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ተከትሎ በአሚባራ ወረዳ ዳይዶ ሳይት የሚገኙ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖች የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቀረቡ።
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአየር ንብረት ለውጥ ሪፎርም ፕሮፎርማሲ ፕሮጀክት በየአመቱ ታላቁን ረመዳን ፆም አስመልክቶ አቅም ለሌላቸው የሙስሊም ማህበረሰብ ክፍሎች ለኢፍጣር የሚሆንና የ2017 የኢድ አልፈጥር በዓልን አስመልክቶ ላደረገላቸው ድጋፍ ተጎጆዎቹ ወቅቱን የጠበቀ ድጋፍ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት