የግሪን ኮል ቴክኖሎጂ ለኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪ አማራጭ የባዮማስ ኢነርጂን ለመጠቀም እድል ይፈጥራል (አቶ ዳንኤል ኦላኒ)
መጋቢት 23/7/2017ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒሰቴር በአምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ አማራጭ የተርማል ኢነርጂ አጠቃቀምን ከማበረታታት አንጻር በሚሰራቸው ስራዎች ከግሪን ኮል ኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ጋር በመተባበር የግሪን ኮል ቴክኖሎጂን የማስተዋወቂያ ሴሚናር እያካሄደ ነው፡፡
ባዮማስ መጠቀም በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ውስጥ ሚና የጎላ መሆኑን የገለፁት በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የመሰረተ ልማትና ግብዓት ዘርፍ አማካሪ አቶ ዳንኤል ኦላኒ ባዮማስ ከኤሌክትሪክ፣ ከፀሃይ እና ከንፋስ ሃይል ቀጥሎ የኢንዱስትሪዎችን የአየር ንብረት ተፅዕኖን ለመቀነስ ቁልፍ ነው፡፡
ኢትዮጵያ በባዮማስ ሀብት ተደራሽ የሆነች ሀገር ነች፣ ወራሪ ተክሎች በሚሊዮን የሚቆጠር ሄክታር መሬት የወረሩ፣ በገጠር የሚገኙ የግብርና ተረፈ ምርቶች፣ በኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ያሉ የግብርና ኢንዱስትሪ ቆሻሻዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ እምቅ የባዮማስ ምንጮች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
የኢንዱስትሪዎችን የካርቦን ልቀት መቀነስ ምርቶች በገበያ ላይ ያላቸውን ተወዳዳሪነት ይጨምራል ያሉት አማካሪው የግሪን ኮል ቴክኖሎጂ ለኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪ አማራጭ የባዮማስ ኢነርጂን ምንጭነት ለመጠቀም እድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡
ዛሬ የሚተዋወቀው የግሪን ኮል ቴክኖሎጂ አሁን ባለው የባዮማስ አቅርቦት ሰንሰለት እና የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ያሳድጋል ያሉት አቶ ዳንኤል በተለያዩ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የባዮማስ ምርትን ለመጠቀም አማራጭ ዕድል እንደሚፈጥር አስረድተዋል፡፡
የግሪን ኮል ተክኖሎጂ የግሪን ሃውስ ጋዝ ልቀት በመቀነስ በካርቦን ግብይት ገበያ ላይ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ገልፀዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት