በጋራ ከሰራን የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደምንችል ባለፉት ሁለት ዓመታት የተሰራው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ኤክስፖ ማሳያ ነው ። (አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ )
መጋቢት 24/2017ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የንቅናቄ መድረኩ ላይ እንደገለፁት በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2017 አሴት የተጨመረባቸውና ጥራት ያላቸው አዳዲስ ምርቶች የሚታዩበት እንደሚሆን ይጠበቃል ብለዋል፡፡
በጋራ ከሰራን የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደምችል ባለፋት አመታት የተሰሩ ስራዎች እና የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ኤክስፖ ትልቅ ማሳያ ነው ፡፡
መንግስት ለአምራች ኢዱስትሪው ከፍተኛ ትኩረት በመሰጠቱ የነበረበትን የተለያዩ ችግሮች የአምራች ኢዱስትሪ ካውስል በማቋቋም ችግሮቹን በመፍታት እየሰራን ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በዚህም ዘርፉ ለሀገር ዕድገት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ገልፀዋል ።
የሕግና የአሠራር ሁኔታዎች መሻሻላቸው ለዕድገቱ ምቹ ሁኔታ መፍጠራቸውን የጠቆሙት አቶ ታረቀኝ አዲሱ የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ተወዳዳሪነትን የሚጨምር ስለመሆኑም አንስተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ አምራቹ ራሱን ለሃገር ውስጥም ሆነ ለዓለም ዓቀፍ ገበያ ራየሚያስተዋውቅበት፤ እርስ በርስ የገበያ ትስስር የሚፈጥርበት እና የተለያዩ ልምድና ተሞክሮዎች የሚያገኝበት ነው ብለዋል ።
ኤክስፖው አዳዲስ ምርቶችን የምናስተዋውቅበት እና እንደሃገር ብራንድ የራስችን የምንገነባበት መሆኑን በመጥቀስ እንደ ሃገር ትልቅ ኢኮኖሚዊ ለወጥ የምናመጣበት ነው ።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት