የህዳሴ ግድቡ የአምራች ኢንዱስሪውን የኃይል አቅርቦት የመፍታትና ተወዳዳሪነቸውን የማሳደግ አቅም አለው

መጋቢት 25/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የህዳሴ ግድብ የአምራች ኢንዱትሪውን የኃይል አቅርቦት ችግር በመቅረፍ ተወዳሪነታቸውን የማሳደግ ትልቅ አቅም አለው ሲሉ የኢንዱትሪ ሚኒስትር ሚኒስትረ ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ ገልጸዋል፡፡

ባለው ነባራዊ ሁኔታ በአምራች ኢንዱስትሪዎች እያጋጠመ ያለውን የሃይል አቅርቦት ችግር በልዩ ትኩረት የመፍታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው ግድቡ ሲጠናቀቅ ከሚያመነጨው ከፍተኛ የኃይል አቅርቦት ለአምራች ኢንዱትርዎች በአነስተኛ ዋጋ የሚቀርብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለአምራች ኢንዱስትሪው ትልቅ ብስራት መሆኑንና የሃይል አቅርቦት ችግሮች በመቅረፍ ተወዳዳሪነታቸውን በማሳደግ እንዲሁም የኃይል አቅርቦትን ተገማች በማድረገ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ሲሉ አክለዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post