የተወሰዱ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ምቹ መደላድልን የፈጠሩ ናቸው (አቶ ታረቀኝ )

መጋቢት 25/2017 ዓ.ም (ኢሚ )መንግስት ላለፉት አመታት ተግባር ላይ ባዋለው የብዝሃ ዘርፍ የኢኮኖሚ እድገት አማራጭ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል ያሉት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ በዚህም ትኩረት ከተሰጣቸው እና ለውጥ ካመጡ ዋና ዋና ዘርፎች መካከል አንዱ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ትኩረቱ አምራች ኢንዱስሪ ዘርፍ የራሱ የሆነ ግልጽ እሳቤና ራዕይ እንዲኖረው ከማድረግ ጀምሮ እንደተሰራበት የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው ዘርፉ የሚመራባቸው የራሱ የሆነ የህግ ማዕቀፎች፣ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና ማስፈጸሚያ መመሪያዎች እንዲሁም የዘርፉ ችግሮች በቅንጅት የሚፈታበት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተግባራዊ በማድረግ አበረታች ውጤቶች መገኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

የዘርፉን እድገት በተመለከተም በ2014 የ4.8 በመቶ፣ በ 2015 የ 7 በመቶ እና በ 2016 የ10.1 በመቶ እድገት ማስመዝገቡን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው በ 2017 በጀት አመትም የ12.8 በመቶ እድገት ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑንም አክለዋል፡፡

ዘርፉ ላስመዘገበው የእስካሁኑ እድገትም እንደ ሀገርም ላለፉት አመታት የተወሰዱ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች አዎንታዊ ሚና መጫወታቸውን እና ምቹ መደላድልን ፈጥረዋል ሲሉ ጠቁመዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post