የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለአምራች ኢንዱስትሪው ማንቂያ ደውል ነው (ዲዛይነር ማርስአለም ሁሴን)

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተግባራዊ ከሆነ ጀምሮ የአምራች ኢንዱስትሪውን ችግሮች በመፍታት ተወዳዳሪነታቸው እንዲያድግ ትልቅ አስተዋፅኦ ማበርከቱን በተለያየ ዘርፈ የተሰማሩ የአምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ገለፁ።

ወ/ሮ ማርስአለም ሁሴን በጨርቃጨርቅና አልባሳት ዘርፍ ተሰማርታ ለዜጎች የስራ እድል የፈጠረች የባህል አልባሳትና ዕደጥበብ አምራች ስትሆን የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የመስሪያ ካፒታልን ጨምሮ፣ የምርት ግብዓት አቅርቦት፣ የማምረት አቅም፣ የገበያ ትስስር እና የመስሪያ ሼድ ችግሮቻቸውን እንደቀረፈላቸው ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለአምራች ኢንዱስትሪው እንደማንቂያ ደውል ነው ያሉት ዲዛይነሯ በንቅናቄው የተገኙ አበረታች ውጤቶችን አጠናክረው በማስቀጠል ራሳቸውን ፣ አምራች ዜጋውን እና በሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገት ላይ የበለጠ አስተዋፅዖ ለማበርከት አትኩረው እየሰሩ መሆኑን አክለዋል።

Share this Post