የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የኢትዮጵያ ምርት በሃገር ውስጥ ሆነ በዓለም አቀፍ ገበያ ተመራጭ እና ተወዳዳሪ እንዲሆን ለማድረግ ዋናውና ተመራጩ መንገድ ነው (አቶ መላኩ አለበል)

ሚያዚያ 22/2017ዓ.ም (ኢሚ) የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ከሚያዚያ 25 እስከ 29/2017ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚገኘው አዲስ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማእከል እንደሚካሄድ የገለፁት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር አቶ መለኩ አለበል የኤክስፖ ዋና አላማ የኢትዮጵያን ምርት ማስተዋወቅ፣ የተሻለ ገበያ እንዲያገኙ ማድረግ፣ ህብረተሰቡ በሃገር ውስጥ ምርት የመጠቀም ልምድ እንዲዳብር ፣ የገበያ ትስስር ለመፍጠር፣ የምርት ጥራት ለማሻሻል፣ ፈጠራን ለማበረታታት እና ለቴክኖሎጂ ሽግግር እና ልምድ ልውውጥ መፍጠር መሆኑን ገልፀዋል ፡፡

የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የኢትዮጵያ ምርት በሃገር ውስጥ ሆነ በዓለም አቀፍ ገበያ ተመራጭ እና ተወዳዳሪ እንዲሆን ለማድረግ ዋናውና ተመራጩ መንገድ ነው ያሉት አቶ መላኩ ኤክስፖው በሁሉም ክልሎች እንዲደረግ በኢትዮጵያ የሚመረቱ ምርቶችን እንዲያውቁ የማስተዋወቅ ስራ ከአንድ መቶ ስልሳ ስምንት በላይ መድረኮች አዘጋጅተን እስከ ወረዳ ድረስ አወያይተናልም ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ እንደገለፁት በዚህ ኤክስፖ ምርቶችን በዓይነት እና በጥራት ማግኘት የሚቻልበት ሲሆን በተጨማሪም የኢንዱስትሪውን ማነቆ የሚፈታ የፓናል ውይይት ፤ማክሮ ኢኮኖሚው ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ምን አስተዋፆኦ አለው ፣ተወዳዳሪ ምርት ለማመረት ምን እናድርግ፣ በኢትዮጵያ ታምርት በሎጀስቲክ እና በፋይናስ ዙሪያ እና በሌሎችም በዘርፉ በተመረጡ ባለሙያዎች ውይይት እና የመፍትሄ አማራጮች እንደሚቀርቡ ገልጸዋል ፡፡

በሌላ በኩል የፈጠራ እና ስታርት አፕ፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ የምርት ልማት ውድድሮች በዘርፉ የተሰማሩ ተቋቋማትን የእውቅ እና የማበረታቻ ሽልማቶች እንደሚኖሩ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገልፀዋል ፡፡

በመጨረሻም በዚህ ኤክስፖ ከሁለት መቶ ሰማንያ ስምንት በላይ ኢንዱስትሪዎች እንደሚሳተፉ የገለፁት ሚኒስትሩ ከአራት ቢሊየን ብር በላይ ግብይት ይከናወናል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል ፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post