አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችን ለሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ያላቸውን አበርክቶ ከፍ ለማድረግ ያለመ ውይይት ተካሄደ።

ሚያዚያ 27/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2017 የሶስተኛው ቀን ውሎ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፈጣን ዕድገት እንዲያመጡ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችል አቅም ለመፍጠር ያለመ ፓናል ውይይት ተካሄደ።

በውይይቱ መነሻ ሀሳብ ያቀረቡት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታህ የሱፍ እንደገለፁት የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ምርታማነት እና ፈጠራ የሚያሳድጉበት ስትራቴጂ ላይ በጋራ መምከር፣ ተግዳሮቶች የሚፈቱበት አቅጣጫ ማሰቀመጥ እና ወደፊት በሚኖራቸው ሚና ላይ የጋራ መግባባት መድረስና የሚጠበቅብንን ኃላፊነት መወጣት ይጠበቅብናል ብለዋል።

ሁላችንም በየዘርፋችን በምናወጣቸው ደንቦችና ህጉችን አነሰተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ታሳቢ አድርገን ከሠራን ፣ ፋይንስ ተደራሽ የሚሆኑበትን መንገድ ካመቻቸን፣ አቅማቸውን በስልጠናና በትምህርት መደገፍ ከተቻልን፣ በቴክኖሎጂ እንዲታገዙ ዲጂታል የአሰራር ሰርዓት እዲኖራቸው ለማድረግ ከሰራን፣ ሰፊ የገበያ ዕድል እንዲመቻች ካደረግን፣ ከሰፊው የአፍሪካ ነፃ የንግድ ገበያ በመግባት ተወዳዳሪ የሚሆኑበትን ዕድል ካመቻቸን በ10 ዓመት የልማት ግባችን ከኢንዱስትሪው 9 ሚሊየን የስራ ዕድሎችን መፍጠር እና 10 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት የያዝነውን ዕቅድ ማሳካት እንደምንችል በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፓ 2017 ላይ የቀረቡ ምርቶችና የቴክኖሎጅ ውጤቶች ማረጋገጫዎች ናቸው ብለዋል።

በፓናል ውይይቱ ላይ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ የግሉ ዘርፍ ተወካዮች ተሳትፈዋል ።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post