የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪ ምርቶችን ተወዳዳሪነት አሳድጓል፡፡(አምባሳደር ግርማ ብሩ)

ሚያዝያ 27/2017 (ኢሚ) የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪ ምርቶች ተወዳዳሪነት እንዲጨምር ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 3ኛውን የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በይፋ መክፈታቸው ይታወቃል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ ኤክስፖውን ጎብኝተዋል።

ጉብኝቱን አስመልክቶ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ በሰጡት ማብራሪያ ኢትዮጵያ ታምርት የሀገር ውስጥ ምርታማነት እንዲጨምር ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል ብለዋል።

የኢንዱስትሪ ዘርፉ የሚያስገኘውን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ለማጉላት በመንግስት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ውጤት እያመጡ መሆናቸውን በኤክስፖው መመልከታቸውንም ተናግረዋል።

ዘርፉ ያለበትን የፋይናንስና መሰል ችግሮችን በመቅረፍ ረገድ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱንም አክለዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በዋናነት ትኩረት ካደረገባቸው ዘርፎች መካከል የኢንዱስትሪ ምርታማነትን መጨመር አንዱ መሆኑን ያብራሩት አማካሪው በዚህም አበረታች ውጤት መመዝገብ ተችሏል ነው ያሉት።

ሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪ ምርቶችን ተወዳዳሪነት ማሳደጉንም አንስተዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post