የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢንዱስትሪ ዘርፉ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር አድርጓል (አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ)

ሚያዚያ 28/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የሚዲያ ግንኙነት ክትትልና መረጃ ማደራጃ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ተስፋሁን ጎዛይ ሶስተኛውን የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ በጎበኙበት ወቅት እንደገለፁት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢንዱስትሪ ዘርፉ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር አድርጓል ብለዋል።

ሀገሪቱ ያላትን እምቅ ሃብት ወደ ጥቅም የመቀየር ልምድ እየዳበረ መምጣቱ የንቅናቄውን ውጤታማነት የሚያረጋግጥ ነው ያሉት አቶ ተስፋሁን ንቅናቄው የታለመለትን ግብ እንዲመታ የመገናኛ ብዙሃን አስተዋጽኦ ጉልህ መሆኑንተናግረዋል ።

በመሆኑም ዘርፉን በማስተዋወቅና የተደራሽነት አድማሱን በማስፋት ሚናቸውን አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው አጽንኦት ሰጥተው አሳስበዋል።

ለአምስት ቀናት በሚካሄደው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 288 ኢንዱስትሪዎች እየተሳተፉ ሲሆን ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት ይፈፀማል ተብሎ ይጠበቃል።

#እኛም_እንሸምት

Share this Post