የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አንዱና ወሳኙ ጉዳይ ለዘረፉ የተቀላጠፈ አገልግሎት መሰጠትና ተወዳዳሪነትን የማሳደግ ተግባር ነው። (አቶ መላኩ አለበል)

ሚያዚያ 28/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2017 የአራተኛው ቀን ውሎን አስመልክቶ ፓናል ውይይቱን በንግግር ሲከፍቱ እንዳሉት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አንዱና ወሳኙ ጉዳይ ለዘረፉ የተቀላጠፈ አገልግሎት መሰጠት እና ተወዳዳሪነትን የማሳደግ ተግባር ብለዋል።

የውይይቱ ርዕሰ ጉዳይ የአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ ያተኩራል ያሉት ሚኒስትሩ ምርት ስናስወጣና ሰናስገባ ከምንወዳደርባቸው ነገሮች አንዱ ሎጀስቲክ፣ ፋይናስ፣ የጉምሩክ ሰርዓት መሆኑን በመጥቀስ የሚስተዋሉ ጥቃቅን ጉድለቶችን በመሙላት ዘርፉን በማዘመንና አሰራሩን ቀልጣፋ በማድረግ ኢንዱስትሪዎችን ለመደገፍ እየተሰራ ነው።

የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ተወዳዳሪና ውጤታማ ለማድረግ የሎጀስቲክና የፋይናስ አገልግሎታችን ቀላል፣ ግልፅ እና የዘመነ መሆን አለበት ብለዋል ።

በፓናል ውይይቱ ላይ ከጉምሩክ ኮሚሽን፣ ከትራንስፓርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር ፣ ከንግድ ባንክ ፣ ከኢዱስትሪ ፓርኮች አሶሴሽን፣ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ከኢትዮጵያ መርከብ እና ሎጀስቲክ አገልግሎት እና ሌሎችም ጉዳዩ የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል ።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post