የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ኢትዮጵያ የማምረት አቅም እና ብሩህ ተስፋ እንዳላት የሚያሳይ ነው (ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ)
ሚያዝያ 28/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ኢትዮጵያ የማምረት አቅም እና ብሩህ ተስፋ እንዳላት የሚያሳይ መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገለጹ።
ለየኢትዮጵያ ፍላጎት ምርታማነትን በመጨመር ጥቅል ሀገራዊ ዕድገትን ማሻሻል መሆኑን ገልጸዋል።
በኤክስፖው የቀረቡት ከቆዳ የተሰሩ የተለያዩ ምርቶች በዓለም አቀፍ የጥራት መመዘኛ መስፈርት ደረጃቸውን ያሟሉ መሆናቸውን መመልከታቸውን ገልፀዋል።
በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶችን ማምረት ከማስቻሉም በላይ የኢትዮጵያን የገበያ መዳረሻ የሚያሰፋ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የአምራች ኢንዱስትሪውን የማምረት አቅም በማሳደግ የሥራ ዕድል የሚፈጥርና ነገ የተሻለ ለማምረት መሰረት የሚጥል መሆኑን ገልጸዋል።
ማምረት የአንድ ሀገር ዕድገት መሰረት መሆኑን የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ በማምረት ላይ የተሰማሩ ሀገራት ከፍ ያለ ዕድገት ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በኤክስፖው የታየው መነቃቃት የማምረት አቅማችንን ያሳድጋል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ ምርቶቹ ኢትዮጵያ የማምረት አቅም እንዳላት እና የነገ ተስፋ የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስጀማሪነት ከሚያዚያ 25 እስከ 29 ቀን 2017 ዓ.ም በሚቆየው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ከ288 በላይ አምራቾች እየተሳተፉበት ይገኛል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት